ዘፍጥረት 31:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)52 እኔ ወደ አንተ ይህን ክምር እንዳላልፍ፥ አንተም ለክፋት ወደ እኔ ይህን ክምርና ይህን ሐውልት እንዳታልፍ፥ ይህ ክምር እና ይህ ሐውልት ምስክር ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም52 ይህን ክምር ድንጋይ ዐልፌ አንተን ለማጥቃት ላልመጣ፣ አንተም ይህን ክምር ድንጋይና ይህን ሐውልት ዐልፈህ እኔን ለማጥቃት ላትመጣ፣ ይህ ክምር ድንጋይ ምስክር ነው፤ ይህም ሐውልት ምስክር ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም52 እኔ አንተን ለማጥቃት ይህን የድንጋይ ቊልል እንደማላልፍ፥ አንተም እኔን ለማጥቃት ይህን የድንጋይ ቊልልና ይህን የመታሰቢያ ሐውልት እንደማታልፍ፥ ይህ የድንጋይ ቊልልና ይህ የመታሰቢያ ሐውልት ምስክሮች ናቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)52 እኔ ወደ አንተ በክፋት ባልፍ ይህች የድንጋይ ክምር፥ ይህችም ሐውልት በክፉ ነገር ትከተለኝ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)52 እኔ ወደ አንተ ይህችን ክምር እንዳላልፍ አንተም ለክፋት ወደ እኔ ይህችን ክምርና ይህችን ሐውልት እንዳታልፋት ይህች ክምር ምስክር ናት ይህችም ሐውልት ምስክር ናት። ምዕራፉን ተመልከት |