Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 31:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ያዕ​ቆ​ብም የላባ ልጆች ያሉ​ትን ነገር፥ “ያዕ​ቆብ ለአ​ባ​ታ​ችን የሆ​ነ​ውን ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ንም ሁሉ ክብር ከአ​ባ​ታ​ችን ከብት አገኘ” ሲሉ ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የላባ ወንዶች ልጆች፣ “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት እንዳለ ወስዶታል፤ ይህ ሁሉ እርሱ ያካበተውም ሀብት ከአባታችን የተገኘ ነው” እያሉ ሲያወሩ ያዕቆብ ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ያዕቆብም፥ የላባ ልጆች፦ “ያዕቆብ የአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ፥ የአባታችን ከነበረውም ይህንም ሁሉ ሀብት አገኘ” ሲሉ ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የላባ ወንዶች ልጆች “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት ወሰደ፤ ይህን ሁሉ ሀብት ያገኘው ከአባታችን ነው” እያሉ መናገራቸውን ያዕቆብ ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ያዕቆብም የላባ ልጆች ያሉትን ነገር፦ ያዕቆብ ለአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ ይህንም ሁሉ ክብር ከአባታችን ከብት አገኘ ሲሉ ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 31:1
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕ​ቆ​ብም እጅግ ባለ​ጠጋ ሆነ፤ ሴቶ​ችም ወን​ዶ​ችም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ ብዙ ከብ​ትም፤ ላሞ​ችም፥ በጎ​ችም፥ ግመ​ሎ​ችና አህ​ዮ​ችም ሆኑ​ለት።


ያዕ​ቆ​ብም የላ​ባን ፊት አየ፤ እነ​ሆም፥ ከእ​ርሱ ጋር እንደ ዱሮው አል​ሆ​ነም።


ላባም ለያ​ዕ​ቆብ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ለት፥ “ሴቶቹ ልጆች ልጆች ናቸው፤ ወን​ዶ​ቹም ልጆች ልጆች ናቸው፤ መን​ጎ​ቹም ከብ​ቶች ናቸው፤ ይህ የም​ታ​የው ሁሉ የእኔ ነው፤ የል​ጆ​ችም ሀብት ነው፤ ዛሬም በእ​ነ​ዚህ በሴ​ቶች ልጆ​ችና በወ​ለ​ዱ​አ​ቸው ልጆ​ቻ​ቸው ላይ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ?


ለአ​ባቴ በግ​ብፅ ምድር ያለ​ኝን ክብ​ሬን ሁሉ፥ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ት​ንም ሁሉ ንገ​ሩት፤ አባ​ቴ​ንም ወደ​ዚህ ፈጥ​ና​ችሁ አም​ጡት።”


“ቤተ ሰቦቼ እኔ ስራ​ራ​ላ​ቸው፥ ሥጋ​ውን እን​በላ ዘንድ ማን በሰ​ጠን ብለው እንደ ሆነ፥


ፍላ​ጻ​ውን ላከ፥ በተ​ና​ቸ​ውም፤ መብ​ረ​ቆ​ችን አበዛ አወ​ካ​ቸ​ውም።


ቍጣ​ቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥ ጆሮ​ዋም እንደ ደነ​ቈረ እባብ፥


የሚያስታርቅ ሰው የልብ ፈዋሽ ነው፤ ቀናተኛ ልብ ግን ለአጥንት ነቀዝ ነው።


እኔ ድካ​ምን ሁሉና የብ​ል​ሃት ሥራ​ውን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ ለሰ​ውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቅን​አ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ሲኦ​ልም ሆድ​ዋን አስ​ፍ​ታ​ለች፤ አፍ​ዋ​ንም ያለ ልክ ከፍ​ታ​ለች፤ የተ​ከ​በ​ሩና ታላ​ላቅ ሰዎች ባለ​ጠ​ጎ​ቻ​ቸ​ውና ድሆ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እር​ስዋ ይወ​ር​ዳሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ባለ​ጠ​ጋም በብ​ል​ጥ​ግ​ናው አይ​መካ፤


“እነሆ በም​ሳሌ የሚ​ና​ገር ሁሉ፥ እንደ እና​ቲቱ እን​ዲሁ ልጅቱ ናት፤ እያለ ምሳሌ ይመ​ስ​ል​ብ​ሻል።


ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፤ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ


በትዕቢት ተነፍቶአል፤ አንዳችም አያውቅም፤ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፤ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።


“ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች