Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 1:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ፥ ለሰ​ማ​ይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ለም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ሁሉ ሐመ​ል​ማሉ ሁሉ መብል ይሁ​ን​ላ​ችሁ።” እን​ዲ​ሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እንዲሁም ለምድር አራዊት ሁሉ፣ ለሰማይ ወፎች ሁሉ፣ በምድር ላይ ለሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ” እንዳለውም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ለምድርም አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው፥” እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እንዲሁም በምድር ላይ ለሚኖሩ እንስሶች ሁሉ፥ በሰማይ ለሚበርሩ ወፎች ሁሉ፥ በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ ለሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ፥ በአጠቃላይ የሕይወት እስትንፋስ ላለው ፍጥረት ሁሉ ምግብ እንዲሆናቸው ልምላሜ ያለውን ሣርና ቅጠል ሁሉ ሰጥቻቸዋለሁ።” እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ለምድርም አራዊት ሁሉ ለሰማይም ወፎች ሁሉ ሕያዉ ነፍስ ላላቸዉ ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸዉ እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 1:30
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሚ​በ​ላ​ውም የመ​ብል ዓይ​ነት ሁሉ ለአ​ንተ ውሰድ፤ ወደ አንተ ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ፤ እር​ሱም ለአ​ንተ፥ ለእ​ነ​ር​ሱም መብል ይሆ​ናል።”


ሕይ​ወት ያለው ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ መብል ይሁ​ና​ችሁ፤ ሁሉ​ንም እንደ ለመ​ለመ ቡቃያ ሰጠ​ኋ​ችሁ።


ጫጭ​ቶ​ቹም ወደ ደም ይሮ​ጣሉ፥ በድን ወደ አለ​በ​ትም ስፍራ ወዲ​ያ​ውኑ ይደ​ር​ሳሉ።”


ልጆ​ቻ​ቸው ያመ​ል​ጣሉ። ይባ​ዛሉ፥ ይዋ​ለ​ዳ​ሉም። ይወ​ጣሉ፥ ወደ እነ​ር​ሱም አይ​መ​ለ​ሱም።


ተራ​ራ​ውን እንደ መሰ​ም​ሪ​ያው ይመ​ለ​ከ​ተ​ዋል፥ ለም​ለ​ሙ​ንም ሁሉ ይፈ​ል​ጋል።


“እነሆ፥ በአ​ንተ ዘንድ የዱር አውሬ አለ፤ እንደ በሬ ሣር ይበ​ላል።


ወደ ረዥም ተራራ በወጣ ጊዜም በሜ​ዳው ላሉ እን​ስ​ሳት በጥ​ልቁ ስፍራ ደስ​ታን ያደ​ር​ጋል።


ሰው ግፍ ያደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ተ​ወም፥ ስለ እነ​ር​ሱም ነገ​ሥ​ታ​ቱን ገሠጸ።


ለሌ​ሎች አሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ገም፥ ፍር​ዱ​ንም አል​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች