Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 1:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ለምድርም አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው፥” እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እንዲሁም ለምድር አራዊት ሁሉ፣ ለሰማይ ወፎች ሁሉ፣ በምድር ላይ ለሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ” እንዳለውም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እንዲሁም በምድር ላይ ለሚኖሩ እንስሶች ሁሉ፥ በሰማይ ለሚበርሩ ወፎች ሁሉ፥ በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ ለሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ፥ በአጠቃላይ የሕይወት እስትንፋስ ላለው ፍጥረት ሁሉ ምግብ እንዲሆናቸው ልምላሜ ያለውን ሣርና ቅጠል ሁሉ ሰጥቻቸዋለሁ።” እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ፥ ለሰ​ማ​ይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ለም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ሁሉ ሐመ​ል​ማሉ ሁሉ መብል ይሁ​ን​ላ​ችሁ።” እን​ዲ​ሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ለምድርም አራዊት ሁሉ ለሰማይም ወፎች ሁሉ ሕያዉ ነፍስ ላላቸዉ ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸዉ እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 1:30
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።”


ከዚህ በፊት የአትክልት ዓይነቶችን ምግብ አድርጌ እንደሰጠኋችሁ እነዚህንም ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ ምግብ እንዲሆኑአችሁ ሰጥቻችኋለሁ።


ጫጩቶቹም ደም ይጠጣሉ፥ በድን ባለበትም ስፍራ እርሱ በዚያ አለ።”


ልጆቻቸው ይጠነክራሉ፥ በሜዳም ያድጋሉ፥ ይወጣሉ፥ ወደ እነርሱም አይመለሱም።


ተራራውን እንደ መሰማርያው ይቃኘዋል፥ ለምለሙንም ሣር በሙሉ ይፈልጋል።


አንተን እንደሠራሁ የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፥ እንደ በሬ ሣር ይበላል።


የሜዳ እንስሶች ሁሉ የሚጫወቱበት ተራራ ምግብን ያበቅልለታል።


እንጀራን ከምድር ያወጣ ዘንድ ሣርን ለእንስሳ፥ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም ያበቅላል።


ለእንስሶችም ምግባቸውን ይሰጣል ለሚጠሩት ለቁራዎች ጫጩቶችም እንዲሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች