Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ምድ​ርም በየ​ዘሩ፥ በየ​ወ​ገ​ኑና በየ​መ​ልኩ የሚ​ዘራ ቡቃ​ያን፥ በም​ድር ላይ በየ​ወ​ገኑ ዘሩ በው​ስጡ የሚ​ገ​ኘ​ው​ንና ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ዛፍ አበ​ቀ​ለች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ምድር ዕፀዋትን፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በውስጣቸው ዘር ያለባቸው ፍሬ የሚያፈሩትን ዛፎች በየወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚህ ዐይነት ምድር አትክልትን፥ በየዐይነቱ የእህል አዝርዕትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን አበቀለች፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 1:12
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “ምድር በየ​ዘሩ፥ በየ​ወ​ገ​ኑና በየ​መ​ልኩ ዘር የሚ​ሰጥ ቡቃ​ያን፥ በም​ድ​ርም ላይ በየ​ወ​ገኑ ዘሩ በው​ስጡ የሚ​ገ​ኘ​ው​ንና ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ዛፍ ታብ​ቅል” አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።


ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ። ሦስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


ሰው ግፍ ያደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ተ​ወም፥ ስለ እነ​ር​ሱም ነገ​ሥ​ታ​ቱን ገሠጸ።


ምድ​ርም ቡቃ​ያ​ውን እን​ደ​ም​ታ​ወጣ፥ ገነ​ትም ዘሩን እን​ደ​ሚ​ያ​በ​ቅል፥ እን​ዲሁ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅ​ንና ደስ​ታን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ያበ​ቅ​ላል።


ምድሪቱም አውቃ በመጀመሪያ ቡቃያ ኋላም ዛላ ኋላም በዛላው ፍጹም ሰብል ታፈራለች።


ዛፍ ሁሉ ከፍ​ሬው ይታ​ወ​ቃል፤ ከእ​ሾህ በለ​ስን አይ​ለ​ቅ​ሙም፤ ከደ​ን​ደ​ርም ወይ​ንን አይ​ለ​ቅ​ሙም።


እርሱ ዘርን ለዘሪ ይሰ​ጣል፤ እህ​ል​ንም ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ያበ​ዛ​ላ​ች​ኋል፤ የጽ​ድ​ቃ​ች​ሁ​ንም መከር ያበ​ጃል።


አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ዘ​ብት አይ​ኑር፤ ሰውም የሚ​ዘ​ራ​ውን ያጭ​ዳል።


ምድ​ርም በእ​ር​ስዋ የሚ​ወ​ር​ደ​ውን ዝናም ከጠ​ጣች፥ ያን​ጊዜ ስለ እርሱ ያረ​ሱ​ላ​ትን መላ​ካም ቡቃያ ታበ​ቅ​ላ​ለች፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘን​ድም በረ​ከ​ትን ታገ​ኛ​ለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች