Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “ምድር በየ​ዘሩ፥ በየ​ወ​ገ​ኑና በየ​መ​ልኩ ዘር የሚ​ሰጥ ቡቃ​ያን፥ በም​ድ​ርም ላይ በየ​ወ​ገኑ ዘሩ በው​ስጡ የሚ​ገ​ኘ​ው​ንና ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ዛፍ ታብ​ቅል” አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር፣ “ምድር ዕፀዋትንም፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በምድር ላይ ዘር ያዘሉ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” አለ፤ እንዳለውም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እግዚአብሔርም፦ “ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል” አለ፥ እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር አትክልትን፥ የእህል አዝርዕትን፥ ፍሬ የሚያፈሩ የፍሬ ዛፎችንና ተክሎችን በየዐይነቱ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እግዚአብሔርም፤ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 1:11
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምድ​ርም በየ​ዘሩ፥ በየ​ወ​ገ​ኑና በየ​መ​ልኩ የሚ​ዘራ ቡቃ​ያን፥ በም​ድር ላይ በየ​ወ​ገኑ ዘሩ በው​ስጡ የሚ​ገ​ኘ​ው​ንና ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ዛፍ አበ​ቀ​ለች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆ​ና​ችሁ ዘንድ በየ​ዘሩ የሚ​ዘ​ራ​ው​ንና የሚ​በ​ቅ​ለ​ውን፥ በም​ድር ሁሉ ላይ የም​ት​ዘ​ሩ​ትን የእ​ህል ፍሬ፥ ዘሩ በው​ስጡ ያለ​ውን ቡቃያ፥ በየ​ፍ​ሬ​ውም የሚ​ዘ​ራ​ውን ዛፍ ሁሉ ሰጠ​ኋ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አዳ​ምን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “በገ​ነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤


የሜዳ ቍጥ​ቋጦ ሁሉ በም​ድር ላይ ከመ​ኖሩ በፊት፥ የሜ​ዳ​ውም ቡቃያ ሁሉ ከመ​ብ​ቀሉ በፊት፥ አዳ​ምም ከመ​ፈ​ጠሩ በፊት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በም​ድር ላይ አላ​ዘ​ነ​በም ነበር፤ ምድ​ር​ንም የሚ​ሠ​ራ​ባት ሰው አል​ነ​በ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለማ​የት ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን፥ ለመ​ብ​ላ​ትም መል​ካም የሆ​ነ​ውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከም​ድር አበ​ቀለ፤ በገ​ነ​ትም መካ​ከል የሕ​ይ​ወ​ትን ዛፍ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ሳ​የ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀ​ው​ንም ዛፍ አበ​ቀለ።


እን​ጀራ ከም​ድር ውስጥ ይወ​ጣል፤ በእ​ሳ​ትም እን​ደ​ሚ​ሆን ታች​ኛው ይገ​ለ​በ​ጣል።


እር​ሱም በውኃ ፈሳ​ሾች ዳር እንደ ተተ​ከ​ለች፥ ፍሬ​ዋን በየ​ጊ​ዜዋ እን​ደ​ም​ት​ሰጥ፥ ቅጠ​ል​ዋም እን​ደ​ማ​ይ​ረ​ግፍ ዛፍ ይሆ​ናል፤ የሚ​ሠ​ራ​ውም ሁሉ ይከ​ና​ወ​ን​ለ​ታል።


ቃሉን ለያ​ዕ​ቆብ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ይና​ገ​ራል።


ምድ​ርም ቡቃ​ያ​ውን እን​ደ​ም​ታ​ወጣ፥ ገነ​ትም ዘሩን እን​ደ​ሚ​ያ​በ​ቅል፥ እን​ዲሁ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅ​ንና ደስ​ታን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ያበ​ቅ​ላል።


በውኃ አጠ​ገብ እንደ ተተ​ከለ፥ በወ​ን​ዝም ዳር ሥሩን እን​ደ​ሚ​ዘ​ረጋ፥ ሙቀ​ትም ሲመጣ እን​ደ​ማ​ይ​ፈራ፥ ቅጠ​ሉም እን​ደ​ሚ​ለ​መ​ልም፥ በድ​ርቅ ዓመ​ትም እን​ደ​ማ​ይ​ሠጋ ፍሬ​ው​ንም እን​ደ​ማ​ያ​ቋ​ርጥ ዛፍ ይሆ​ናል።


አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቍኦረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።


እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?


ምድሪቱም አውቃ በመጀመሪያ ቡቃያ ኋላም ዛላ ኋላም በዛላው ፍጹም ሰብል ታፈራለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እንደ ወደደ አገ​ዳን ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ዘርም አገ​ዳው እየ​ራሱ ነው።


ምድ​ርም በእ​ር​ስዋ የሚ​ወ​ር​ደ​ውን ዝናም ከጠ​ጣች፥ ያን​ጊዜ ስለ እርሱ ያረ​ሱ​ላ​ትን መላ​ካም ቡቃያ ታበ​ቅ​ላ​ለች፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘን​ድም በረ​ከ​ትን ታገ​ኛ​ለች።


ወንድሞቼ ሆይ! በለስ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውሃም ጣፋጭ ውሃ አይወጣም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች