Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እር​ሱም ጸጋን ሰጠ፤ ከቤተ ሰቦ​ቹም ሐዋ​ር​ያ​ትን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነቢ​ያ​ት​ንና የወ​ን​ጌል ሰባ​ኪ​ዎ​ችን፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ንና መም​ህ​ራ​ንን ሾመ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ አንዳንዶቹ ነቢያት፣ አንዳንዶቹም ወንጌል ሰባኪዎች፣ ሌሎቹ ደግሞ እረኞችና አስተማሪዎች ይሆኑ ዘንድ የሰጠ እርሱ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ የሰጠ እርሱ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ አንዳንዶቹ ነቢያት፥ አንዳንዶቹ የወንጌል ሰባኪዎች፥ አንዳንዶቹ የምእመናን እረኞች፥ አንዳንዶቹ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ስጦታዎችን ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 4:11
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እስ​ራ​ኤ​ልም ብዙ ዘመን እው​ነ​ተ​ኛ​ውን አም​ላክ ሳያ​መ​ልኩ፥ ያለ አስ​ተ​ማ​ሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖ​ራሉ።


እንደ ልቤም የሚ​ሆኑ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዕ​ው​ቀ​ትና በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም ይጠ​ብ​ቁ​አ​ች​ኋል።


በአ​ን​ጾ​ኪያ በነ​በ​ረ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ነቢ​ያ​ትና መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም በር​ና​ባስ፥ ኔጌር የተ​ባ​ለው ስም​ዖን፥ የቀ​ሬ​ናው ሉቅ​ዮስ፥ ከአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ከሄ​ሮ​ድስ ጋር ያደ​ገው ምናሔ፥ ሳው​ልም ነበሩ።


አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ወጥ​ተን ወደ ቂሳ​ርያ ሄድን፤ ወደ ወን​ጌ​ላ​ዊው ወደ ፊል​ጶስ ቤትም ገባን፤ እር​ሱም ከሰ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ዲያ​ቆ​ናት አንዱ ነው።


የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ልም በማ​ገ​ል​ገሉ ይትጋ፤ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ርም በማ​ስ​ተ​ማሩ ይትጋ፤


መን​ፈስ ቅዱስ አንድ ሲሆን ስጦ​ታው ልዩ ልዩ ነው።


በነ​ቢ​ያ​ትና በሐ​ዋ​ር​ያት መሠ​ረት ላይ ታን​ጻ​ች​ኋ​ልና የሕ​ን​ጻው የማ​ዕ​ዘን ራስ ድን​ጋ​ይም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው፤


በሌላ ዘመን ለሰው ልጆች ያል​ተ​ገ​ለጠ ዛሬ ለቅ​ዱ​ሳን ሐዋ​ር​ያ​ቱና ለነ​ቢ​ያቱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ እንደ ተገ​ለጠ፥


“ምር​ኮን ማር​ከህ ወደ ሰማይ ወጣህ፤ ጸጋ​ህ​ንም ለሰው ልጅ ሰጠህ” ይላ​ልና።


አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፤ መከራን ተቀበል፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፤ አገልግሎትህን ፈጽም።


መም​ህ​ራን ልት​ሆኑ ሲገ​ባ​ችሁ፥ ካመ​ና​ችሁ ጀምሮ በት​ም​ህ​ርት ላይ የቈ​ያ​ችሁ ስለ ሆነ፥ እስከ ዛሬም ገና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃ​ሉን መጀ​መ​ሪያ ትም​ህ​ርት ሊያ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ችሁ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ወተ​ት​ንም ሊግ​ቱ​አ​ችሁ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ጽኑ ምግ​ብ​ንም አይ​ደ​ለም።


እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


ለከተማይቱም ቅጥር ዐሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፤ በእነርሱም ውስጥ የዐሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች