Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ስለ ሠራ​ች​ሁት ኀጢ​አት ሁሉ፥ እር​ሱ​ንም ለማ​ስ​ቈ​ጣት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ የሆ​ነ​ውን ነገር ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ እንደ ፊተ​ኛው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ዳግ​መኛ ለመ​ንሁ፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፥ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን በመፈጸም ለቍጣ እንዲነሣሣ የሚያደርገውን ኀጢአት ሁሉ ስለ ሠራችሁ፣ እህል ውሃ ሳልቀምስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እንደ ገና በእግዚአብሔር ፊት በግንባሬ ተደፋሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዚህም በኋላ እንደገና አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እህል ሳልቀምስና ውኃ ሳልጠጣ በጌታ ፊት በግንባሬ ተደፍቼ ቆየሁ። ይህንንም ያደረግኹት ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቆጣት በጌታ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጋችሁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚህም በኋላ እንደገና አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ምንም ነገር ሳልበላና ሳልጠጣ በእግዚአብሔር ፊት በግንባሬ ተደፍቼ ቈየሁ። ይህንንም ያደረግኹት እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ኃጢአት ሠርታችሁ እርሱን በማስቈጣታችሁ ምክንያት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18-19 ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቆጣት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጋችሁ፥ እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ ከተቈጣባችሁ ከቍጣውና ከመዓቱ የተነሣ ስለ ፈራሁ፥ እንደ ፊተኛው በእግዚአብሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ወደቅሁ፤ እንጀራ አልበላሁም፥ ውኃም አልጠጣሁም። እግዚአብሔርም በዚያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 9:18
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ስለ ሕፃኑ እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ለመነ፤ ዳዊ​ትም ጾመ፤ ገብ​ቶም በመ​ሬት ላይ ተኛ።


ተነ​ሥ​ቶም በላ፤ ጠጣም፤ በዚ​ያም በበ​ላው የም​ግብ ኀይል እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ።


ዕዝ​ራም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ተነ​ሥቶ ወደ ኤሊ​ያ​ሴብ ልጅ ወደ ዮሐ​ናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምር​ኮ​ኞ​ቹም ኀጢ​አት ያለ​ቅስ ነበ​ርና ገብቶ እን​ጀራ አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም።


በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥


በዚ​ያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበረ፤ እን​ጀ​ራም አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም። በጽ​ላ​ቱም ዐሥ​ሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።


“አቤቱ በፊ​ት​ህስ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አን​ገተ ደን​ዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማ​ማ​ነ​ታ​ች​ንን፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንና በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ ለአ​ን​ተም እን​ሆ​ና​ለን” አለ።


“እኔም እንደ ፊተ​ኛው ጊዜ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በተ​ራ​ራው ላይ ቆምሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚህ ጊዜ ደግሞ ሰማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ አል​ወ​ደ​ደም።


ሁለ​ቱ​ንም ጽላት ያዝሁ፤ ከሁ​ለ​ቱም እጆች ጣል​ኋ​ቸው፤ በእ​ና​ን​ተም ፊት ሰበ​ር​ኋ​ቸው።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ያጠ​ፋ​ችሁ ዘንድ ስለ ተና​ገረ ቀድሞ እንደ ለመ​ንሁ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ንሁ።


ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ባ​ቸ​ውን የቃል ኪዳን ጽላት እቀ​በል ዘንድ ወደ ተራራ በወ​ጣሁ ጊዜ፥ በተ​ራ​ራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀ​ምጬ ነበር፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች