Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እኔ ግን በዚ​ህች ምድር እሞ​ታ​ለሁ። ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም አል​ሻ​ገ​ርም፤ እና​ንተ ግን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ያች​ንም መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እኔም በዚህች ምድር እሞታለሁ፤ ዮርዳኖስን አልሻገርም፤ እናንተ ግን ልትሻገሩ ነው፤ ያችንም መልካም ምድር ትወርሳላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እኔ በዚህች ምድር እሞታለሁና፥ ዮርዳኖስን አልሻገርም፥ እናንተ ግን ትሻገራላችሁ፥ ያችንም መልካሚቱን ምድር ትወርሳላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ስለዚህም እኔ የዮርዳኖስን ወንዝ ሳልሻገር በዚህች ምድር እሞታለሁ፤ እናንተ ግን ተሻግራችሁ እነሆ ያቺን ለምለም ምድር ልትወርሱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እኔ ግን በዚህች ምድር እሞታለሁ፥ ዮርዳኖስንም አልሻገርም፤ እናንተ ግን ትሻገራላችሁ፥ ያችንም መልካሚቱን ምድር ትወርሳላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 4:22
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እኔ ከም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ እና​ን​ተን ብቻ​ች​ሁን አው​ቄ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ እበ​ቀ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


ባየ​ሃ​ትም ጊዜ ወን​ድ​ምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ተጨ​መረ አንተ ደግሞ ወደ ወገ​ንህ ትጨ​መ​ራ​ለህ።


እና​ንተ በጺን ምድረ በዳ በማ​ኅ​በሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋ​ልና፥ በእ​ነ​ር​ሱም ፊት በው​ኃው ዘንድ አላ​ከ​በ​ራ​ች​ሁ​ኝ​ምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃ​ዴስ ያለው የክ​ር​ክር ውኃ ነው።”


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቀል ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንን ተበ​ቀል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ወገ​ኖ​ችህ ትጨ​መ​ራ​ለህ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በእኔ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደ​ዚያ አት​ገ​ባም፤


እኔ እን​ድ​ሻ​ገ​ርና፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ያለ​ች​ውን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር፥ ያንም መል​ካ​ሙን ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር አንጢ ሊባ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳይ ፍቀ​ድ​ልኝ።


ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ር​ምና ወደ ተራ​ራው ራስ ውጣ፤ ዐይ​ን​ህ​ንም ወደ ባሕር ወደ መስ​ዕም፥ ወደ አዜ​ብም ወደ ምሥ​ራ​ቅም አን​ሥ​ተህ በዐ​ይ​ንህ ተመ​ል​ከት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የም​ት​ሞ​ት​በት ቀን እነሆ ቀረበ፤ ኢያ​ሱን ጠር​ተህ እር​ሱን አዝ​ዘው ዘንድ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ቁም” አለው። ሙሴና ኢያ​ሱም ሄደው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ቆሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች