Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እና​ን​ተም ቀር​ባ​ችሁ ከተ​ራ​ራው በታች ቆማ​ችሁ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም እስከ ሰማይ ድረስ በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ጨለ​ማና አውሎ ነፋስ፥ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማም ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ተራራው በጥቍር ደመናና በድቅድቅ ጨለማ ተውጦ ሳለ ነበልባሉ ሰማይ እስከሚደርስ ድረስ በተቃጠለ ጊዜ መጥታችሁ ከተራራው ግርጌ ቆማችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፥ እስከ ሰማይም ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፥ ጨለማም ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “እስከ ሰማይ በሚደርስ የእሳት ነበልባልና ጥቅጥቅ ባለ የጢስ ደመና ወደተጋረደው ተራራ ግርጌ ቀርባችሁ ቆማችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፤ እስከ ሰማይም መካከል ድረስ አሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፤ ጨለማና ደመና ድቅድቅ ጨለማም ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 4:11
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰማ​ዮ​ችን አዘ​ነ​በለ፤ ወረ​ደም፤ ጭጋ​ግም ከእ​ግሩ በታች ነበረ።


ከም​ድር መና​ወጥ በኋላ እሳት ሆነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳቱ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም። ከእ​ሳ​ቱም በኋላ እንደ ፉጨት ያለ ቀጭን ድምፅ ሆነ፤ በዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነበረ።


ባሪ​ያህ ደግሞ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፤ በመ​ጠ​በ​ቁም ብዙ ዋጋ ይቀ​በ​ላል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማዳ​ኑን አሳየ። በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት ቃል ኪዳ​ኑን ገለጠ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “ከአ​ንተ ጋር ስነ​ጋ​ገር ሕዝቡ እን​ዲ​ሰሙ፥ ደግ​ሞም ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ያ​ም​ኑ​ብህ፥ እነሆ፥ በዐ​ምደ ደመና ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ” አለው። ሙሴም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ተና​ገ​ራ​ችሁ፤ የቃ​ልን ድምፅ ሰማ​ችሁ፤ ከድ​ምፅ በቀር መል​ክን ግን አላ​ያ​ች​ሁም።


“እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በእ​ሳት መካ​ከል ድም​ፁን በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ፥ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ሲነ​ድድ እና​ንተ፥ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ችሁ አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም፥ ወደ እኔ ቀረ​ባ​ችሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች