Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ይኸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ነው። ከዚ​ያም በኋላ ሁላ​ችሁ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ርስት ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ይኸውም፣ እግዚአብሔር ለእናንተ እንዳደረገው ሁሉ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፋቸውና አምላካችሁ እግዚአብሔር ከዮርዳኖስ ማዶ የሚሰጣቸውን ምድር እነርሱም እንደዚሁ እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያ በኋላ እያንዳንዳችሁ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ይኸውም ጌታ እናንተን እንዳሳረፈ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ ጌታ አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁሉ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እግዚአብሔር ለእናንተ በዚህ እንዳደረገላችሁ ሁሉ፥ ለእነርሱም ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ በኩል የሚያወርሳቸውን ምድር ሰጥቶ በሰላም እስካሳረፋቸው ድረስ ወገኖቻችሁን እስራኤላውያንን እርዱ፤ ከዚያም በኋላ እኔ ወደ ሰጠኋችሁ ወደዚህች ምድር መመለስ ትችላላችሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ይኸውም እግዚአብሔር እናንተን እንዳሳረፈ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁሉ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 3:20
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ርስ​ታ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ወደ ቤታ​ችን አን​መ​ለ​ስም፤


ምድ​ሪ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ድል እስ​ክ​ት​ሆን ድረስ ከዚ​ያም በኋላ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጹ​ሓን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ይህች ምድ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርስት ትሆ​ና​ች​ኋ​ለች።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ማረ​ፊ​ያና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አል​ደ​ረ​ሳ​ች​ሁ​ምና።


በዚ​ያም ጊዜ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ሁት፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ ነገ​ሥት ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ዐይ​ኖ​ችህ አይ​ተ​ዋል፤ እን​ዲሁ በም​ታ​ል​ፍ​ባ​ቸው መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋል።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በፀ​ሐይ መውጫ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ት​ማ​ላ​ችሁ።”


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ ሰም​ታ​ች​ኋል፤ እኔም ላዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ነገር ሁሉ ታዝ​ዛ​ች​ኋል፤


አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አሳ​ር​ፎ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ተመ​ለሱ፤ ወደ ቤታ​ች​ሁና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ሂዱ።


“በብዙ ብል​ጥ​ግና፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ከብት፥ በብ​ርም፥ በወ​ር​ቅም፥ በና​ስም፥ በብ​ረ​ትም፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ የጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ምርኮ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር ተካ​ፈሉ።”


የሮ​ቤ​ልም ልጆች የጋ​ድም ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ሄዱ፤ በሙ​ሴም እጅ በተ​ሰጠ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ወደ ተቀ​በ​ሉት ወደ ርስ​ታ​ቸው ወደ ገለ​ዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከ​ነ​ዓን ምድር ካለ​ችው ከሴሎ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ተመ​ለሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች