Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 3:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በዚ​ያም ጊዜ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ሁት፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ ነገ​ሥት ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ዐይ​ኖ​ችህ አይ​ተ​ዋል፤ እን​ዲሁ በም​ታ​ል​ፍ​ባ​ቸው መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በዚያ ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ስል አዘዝሁት፤ “አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ በገዛ ዐይንህ አይተሃል፤ አሁንም ዐልፈህ በምትሄድባቸው መንግሥታት ላይ ሁሉ እግዚአብሔር ይህንኑ ይደግመዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኢያሱንም ያንጊዜ አዘዝኩት፦ “ጌታ አምላካችሁ በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ያደረገውን ሁሉ ዐይኖችህ አይተዋል፥ እንዲሁ ሁሉ በምታልፍባቸው መንግሥታት ላይ ጌታ ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ከዚህም ቀጥሎ ኢያሱን እንዲህ ስል መከርኩት፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችሁ ሲሖንና ዖግ ተብለው በሚጠሩት በሁለት ነገሥታት ያደረገውን በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ምድሩን በምትወርሱበት በማንኛውም ሕዝብ ላይ ይህንኑ ተመሳሳይ ድርጊት ይደግመዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በዚያም ጊዜ ኢያሱን፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥት ያደረገውን ሁሉ ዓይኖችህ አይተዋል፤ እንዲሁ በምታልፍባቸው መንግሥታት ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 3:21
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስም​ህን የሚ​ወዱ ሁሉ በአ​ንተ ይታ​መ​ናሉ፥ አቤቱ፥ የሚ​ሹ​ህን አት​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምና።


እር​ሱም እን​ዲህ ካለ ሞት አዳ​ነን፤ ያድ​ነ​ን​ማል፤ አሁ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ነን እር​ሱን እን​ታ​መ​ና​ለን።


ስለ​ዚ​ህም ስለ ክር​ስ​ቶስ መከራ መቀ​በ​ልን፥ መሰ​ደ​ብን፥ መጨ​ነ​ቅን፥ መሰ​ደ​ድን፥ መቸ​ገ​ር​ንም ወደ​ድሁ፤ መከራ በተ​ቀ​በ​ልሁ ጊዜ ወዲ​ያ​ውኑ እበ​ረ​ታ​ለ​ሁና።


በከ​ሃ​ሊ​ነቱ እንደ ረዳን መጠን፥ የም​ና​ስ​በ​ው​ንና የም​ን​ለ​ም​ነ​ውን ሁሉ ትሠሩ ዘንድ፥ ታበ​ዙም ዘንድ ሊያ​ጸ​ና​ችሁ ለሚ​ችል፥


ይኸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ነው። ከዚ​ያም በኋላ ሁላ​ችሁ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ርስት ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ስለ እና​ንተ ይዋ​ጋ​ልና ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ አት​ፍሩ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓይ​ንህ እያ​የች፥ ታላቅ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ ምል​ክ​ት​ንም፥ ተአ​ም​ራ​ት​ንም፥ የጸ​ና​ች​ው​ንም እጅ፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ው​ንም ክንድ አድ​ርጎ እን​ዳ​ወ​ጣህ፤ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ያደ​ር​ጋል።


ኢያ​ሱም፥ “በም​ት​ወ​ጉ​አ​ቸው በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ሁሉ ላይ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋ​ልና አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግጡ፤ ጽኑ፤ አይ​ዞ​አ​ችሁ” አላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች