Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 20:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሚስ​ትም አጭቶ ያላ​ገ​ባት ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ገ​ባት ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ አለዚያ በጦርነቱ ይሞትና ሌላ ሰው ያገባታል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ ያለበለዚያ በጦርነቱ ይሞትና ሌላ ሰው ያገባታል።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሚስት ለማግባትስ ልጃገረድ ያጨ ሰው አለን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ ያለበለዚያ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት እርሱ ያጫት ልጃገረድ ለሌላ ሰው ሚስት ትሆናለች።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሚስትም አጭቶ ያላገባትም ሰው ቢኖር በሰልፍ እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያገባት ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 20:7
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።


ወይ​ንም ተክሎ ደስ ያል​ተ​ሰ​ኘ​በት ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው ደስ እን​ዳ​ይ​ሰ​ኝ​በት ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።


“አዲስ ሚስ​ትም ያገባ ሰው ወደ ጦር​ነት አይ​ሂድ፤ ምንም ነገር አይ​ጫ​ኑ​በት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈ​ቃዱ ይቀ​መጥ፤ የወ​ሰ​ዳ​ት​ንም ሚስ​ቱን ደስ ያሰ​ኛት።


ሚስት ታገ​ባ​ለህ፤ ሌላም ሰው ይነ​ጥ​ቅ​ሃል፤ ቤት ትሠ​ራ​ለህ፤ በእ​ር​ሱም አት​ቀ​መ​ጥ​በ​ትም፤ ወይን ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ከእ​ር​ሱም አት​ለ​ቅ​ምም።


የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች