Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 18:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ች​ሁ​በት ቀን፦ ‘እን​ዳ​ን​ሞት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ደግሞ አን​ስማ፤ ይህ​ችን ታላቅ እሳት ደግሞ አንይ’ ብላ​ችሁ እንደ ለመ​ና​ች​ሁት ሁሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት፣ “እንዳልሞት የአምላክህ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልስማ፤ እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግሜ አልይ” ብለህ አምላክህን እግዚአብሔርን የጠየቅኸው ይህን ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት፥ ‘እንዳልሞት የጌታ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልስማ፤ እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግሜ አልይ’ ብለህ አምላክህን ጌታን የጠየቅኸው ይህን ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “በሲና ተራራ ላይ በተሰበሰባችሁበት ቀን እሞታለሁ ብለህ በመፍራት እግዚአብሔር ዳግመኛ እንዳይናገርህና የመገለጡን ሁኔታ የሚያመለክተውን አስፈሪ እሳት እንዳታይ ጠይቀህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 18:16
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝ​ቡም ሁሉ ነጐ​ድ​ጓ​ዱ​ንና መብ​ረ​ቁን፥ የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ፥ ተራ​ራ​ው​ንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው ርቀው ቆሙ።


ሙሴ​ንም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ተና​ገር፤ ነገር ግን እን​ዳ​ን​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር አይ​ና​ገር” አሉት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጁን ዘር​ግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “እነሆ፥ ቃሌን በአ​ፍህ ውስጥ አኑ​ሬ​አ​ለሁ፤


“አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረን፦ በዚህ ተራራ መቀ​መ​ጣ​ችሁ በቃ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በተ​ራ​ራው ላይ በእ​ሳት መካ​ከል የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁን ዐሠ​ር​ቱን ቃላት ቀድሞ ተጽ​ፈው እንደ ነበረ በጽ​ላቱ ላይ ጻፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ር​ሱን ለእኔ ሰጠኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፉ​ትን ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ሰጠኝ፤ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ራ​ራው ላይ የነ​ገ​ረኝ ቃል ሁሉ ተጽ​ፎ​ባ​ቸው ነበር።


ወደ መለ​ከት ድም​ፅም፥ ወደ ቃሎ​ችም ነገር አል​ደ​ረ​ሳ​ች​ሁ​ምና፥ ያንም ነገር የሰ​ሙት ሌላ ቃል እን​ዳ​ይ​ጨ​መ​ር​ባ​ቸው ለመኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች