Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ይህም ስለ ልብ ትሕ​ት​ናና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስለ መፍ​ራት፥ ለሥጋ ስለ አለ​ማ​ዘን ጥበ​ብን ይመ​ስ​ላል፤ ነገር ግን ከሥጋ በላይ ነው እንጂ ምንም ክብር የለ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እነዚህ ነገሮች በገዛ ራስ ላይ ከሚፈጥሩት የአምልኮ ስሜት፣ ከዐጕል ትሕትናና ሰውነትን ከመጨቈን አንጻር በርግጥ ጥበብ ያለባቸው ይመስላሉ፤ ነገር ግን የሥጋን ልቅነት ለመቈጣጠር አንዳች ፋይዳ የላቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እነዚህም በገዛ ፈቃድ የሚደረግ አምልኮንና ራስን ማዋረድ ሥጋንም የመጨቆን ጥበብ ያላቸው ይመስላሉ፤ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅሙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እነዚህ ትእዛዞች ከገዛ ፈቃድ በመነጨ አምልኮና በአጉል ትሕትና፥ ሰውነትንም በማጐሳቈል ላይ ስለሚያተኲሩ ጥበብ ያላቸው ይመስሉ ይሆናል፤ ነገር ግን ሥጋዊ ስሜትን በመቈጣጠር ረገድ ዋጋቢሶች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ይህ እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል፥ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 2:23
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ልበ​ሱት፤ የሥ​ጋ​ች​ሁ​ንም ምኞት አታ​ስቡ።


ከቶ ሥጋ​ውን መጥ​ላት የሚ​ቻ​ለው የለም፤ ክር​ስ​ቶስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን እንደ መገ​ባት መግቡ፤ ጠብ​ቁም።


በመ​ታ​ለ​ልና ራስን ዝቅ በማ​ድ​ረግ ለመ​ላ​እ​ክት አም​ልኮ ትታ​ዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአ​ላ​የ​ውም በከ​ንቱ የሥ​ጋው ምክር እየ​ተ​መካ የሚ​ያ​ሰ​ን​ፋ​ችሁ አይ​ኑር።


ይህ ሁሉ እንደ ሰው ትእ​ዛ​ዝና ትም​ህ​ርት ለጥ​ፋት ነውና።


ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግ ያይ​ደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥር​ዐት ለከ​ንቱ የሚ​ያ​ታ​ልሉ ሰዎች በነ​ገር ማራ​ቀቅ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፥ ተጠ​ን​ቀቁ።


እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፤ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል እንዲርቁ ያዝዛሉ።


ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች