Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከዚህ ዓለም ኑሮ ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ታ​ችሁ እን​ደ​ገና በዓ​ለም እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች እን​ዴት ትሠ​ራ​ላ​ችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ለዚህ ዓለም መርሕ ከክርስቶስ ጋራ ከሞታችሁ፣ ታዲያ በዚህ ዓለም እንደሚኖር ለምን ትገዙላቸዋላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ከመሠረታዊው የዓለም ረቂቅ መንፈስ ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥ ከዓለም እንዳልተለያችሁ ዓይነት ኑሮ ለምን ትኖራላችሁ? ለምንስ እንደነዚህ ላሉት ትእዛዞች ትገዛላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከክርስቶስ ጋር ሞታችሁ ከዚህ ዓለም መሠረታዊ ሥርዓቶች ፈጽማችሁ የተለያችሁ ከሆናችሁ ታዲያ፥ አሁን ከዓለም እንዳልተለያችሁ ዐይነት ሆናችሁ ስለምን እንደዚህ ላሉት ትእዛዞች ትገዛላችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20-21 ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 2:20
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ን​ተስ ከዓ​ለም ብት​ሆኑ ዓለም በወ​ደ​ዳ​ችሁ ነበር፤ ዓለም ወገ​ኖ​ቹን ይወ​ዳ​ልና፤ ነገር ግን እኔ ከዓ​ለም መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ ከዓ​ለም አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ዓለም ይጠ​ላ​ች​ኋል።


በሥ​ጋ​ች​ንስ እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን በእ​ር​ሱው ሥር​ዐት የም​ን​ሄ​ድና የም​ን​ዋጋ አይ​ደ​ለም።


እን​ዲሁ እኛም ሕፃ​ናት በነ​በ​ርን ጊዜ፥ ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት ተገ​ዝ​ተን ነበር።


እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መስ​ቀል እንጂ በሌላ አል​መ​ካም፤ በእኔ ዘንድ ዓለሙ የሞተ ነው፥ እኔም በዓ​ለሙ ዘንድ የሞ​ትሁ ነኝ።


ሁለ​ቱ​ንም አድሶ አንድ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ በሥ​ር​ዐቱ የት​እ​ዛ​ዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕር​ቅ​ንም አደ​ረገ።


ከባ​ላ​ጋ​ራ​ችን የተ​ነሣ በት​እ​ዛዝ የተ​ጻ​ፈ​ውን የዕ​ዳ​ች​ንን ደብ​ዳቤ ደመ​ሰ​ሰ​ልን፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ንም አራ​ቀው፤ በመ​ስ​ቀ​ሉም ቸነ​ከ​ረው።


እን​ግ​ዲህ በመ​ብ​ልም ቢሆን፥ በመ​ጠ​ጥም ቢሆን፥ በልዩ ልዩ በዓ​ላ​ትም ቢሆን፥ በመ​ባ​ቻም ቢሆን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቢሆን የሚ​ነ​ቅ​ፋ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ።


እን​ዴ​ትስ ይህን አት​ዳ​ስስ፥ ይህን አት​ንካ፥ ይህ​ንም አት​ቅ​መስ ይሉ​አ​ች​ኋል?


ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግ ያይ​ደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥር​ዐት ለከ​ንቱ የሚ​ያ​ታ​ልሉ ሰዎች በነ​ገር ማራ​ቀቅ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፥ ተጠ​ን​ቀቁ።


እና​ንተ ፈጽ​ማ​ችሁ ሞታ​ች​ኋ​ልና፤ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ሠ​ወ​ረች ናትና።


ሌላ ልዩ ትም​ህ​ርት አታ​ምጡ፤ ልባ​ችሁ በመ​ብል ያይ​ደለ በጸጋ ቢጸና ይበ​ል​ጣ​ልና፤ በዚያ ይሄዱ የነ​በሩ እነ​ዚያ አል​ተ​ጠ​ቀ​ሙ​ምና።


አመንዝሮች ሆይ! ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።


ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች