Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሳውል ግን ገና አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን ይቃ​ወም ነበር፤ የሰ​ው​ንም ቤት ሁሉ ይበ​ረ​ብር ነበር፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እየ​ጐ​ተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስ​ገ​ባ​ቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ታጥቆ ተነሣ፤ ከቤት ወደ ቤት በመግባትም ወንዶችንና ሴቶችን ጐትቶ እያወጣ ወህኒ ቤት ያስገባቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ ነበር፤ ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ይጥር ነበር፤ ከቤት ወደ ቤትም እየገባ ወንዶችና ሴቶች አማኞችን እየጐተተ ያወጣ ነበር፤ ወደ እስር ቤትም ያስገባቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ ነበር፤ ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 8:3
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌቶ​ች​ዋም የም​ታ​ገ​ባ​ላ​ቸው የጥ​ቅ​ማ​ቸው ተስፋ እንደ ቀረ ባዩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስ​ንና ሲላ​ስን ይዘው በገ​በያ እየ​ጐ​ተቱ ወደ ገዢ​ዎች ወሰ​ዱ​አ​ቸው።


እኔም እን​ዲህ አል​ሁት፦ ‘ጌታዬ ሆይ፥ በአ​ንተ የሚ​ያ​ም​ኑ​ትን በየ​ም​ኵ​ራ​ቦ​ቻ​ቸው ሳስ​ራ​ቸ​ውና ስደ​በ​ድ​ባ​ቸው የነ​በ​ርሁ እኔ እንደ ሆንሁ እነ​ርሱ ያው​ቃሉ።


ከከ​ተ​ማም ወደ ውጭ ጐት​ተው አው​ጥ​ተው ወገ​ሩት፤ የሚ​ወ​ግ​ሩት ሰዎ​ችም ልብ​ሳ​ቸ​ውን ሳውል በሚ​ባል ጐል​ማሳ እግር አጠ​ገብ አስ​ቀ​መጡ።


እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስ​ንም ደጋግ ሰዎች አን​ሥ​ተው ቀበ​ሩት፤ ታላቅ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት።


የሰ​ሙ​ትም ሁሉ አደ​ነቁ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይህን ስም የሚ​ጠ​ሩ​ትን ሁሉ ይጠ​ላ​ቸው የነ​በ​ረው ይህ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ዚህ ወደ​ዚህ የመ​ጣው እያ​ሰረ ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?”


ከሐ​ዋ​ር​ያት ሁሉ እኔ አን​ሣ​ለ​ሁና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ስለ አሳ​ደ​ድሁ ሐዋ​ርያ ተብዬ ልጠራ የማ​ይ​ገ​ባኝ፥


በአ​ይ​ሁድ ሥር​ዐት ውስጥ በነ​በ​ርሁ ጊዜ፥ የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ድሞ ሥራ​ዬን ሰም​ታ​ች​ኋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን እጅግ አሳ​ድ​ድና መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው ነበር።


በኦ​ሪት ጽድ​ቅም ያለ ነውር ሆኜ በቅ​ን​ዐት ምእ​መ​ና​ንን አሳ​ድድ ነበር።


አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፤


እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ። ባለ ጠጎቹ የሚያስጨንቁአችሁ አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤትም የሚጎትቱአችሁ እነርሱ አይደሉምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች