Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 18:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ንጉ​ሡም እጅግ ደነ​ገጠ፤ በበ​ሩም ላይ ወዳ​ለ​ችው ሰገ​ነት ወጥቶ አለ​ቀሰ፤ ሲሄ​ድም፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ በአ​ንተ ፋንታ እኔ እን​ድ​ሞት ቤዛ​ህም እን​ድ​ሆን ማን ባደ​ረ​ገኝ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ንጉሡም እጅግ ዐዘነ፤ በቅጽር በሩ ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም ሆይ፤ ልጄን! ወየው ልጄን!” ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ንጉሡም እጅግ አዘነ፤ በቅጽር በሩ አናት ላይ ወደሚገኘውም ክፍል ወጥቶ አለቀሰ፤ ወደዚያም ሲመጣ “ልጄ ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! አቤሴሎም ልጄ! ምነው በአንተ ምትክ እኔ በሞትኩ ልጄ ሆይ! አቤሴሎም ልጄ!” እያለ በመጮኽ ያለቅስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ንጉሡም እጅግ አዘነ፥ በበሩም ላይ ወዳለችው ቤት ወጥቶ አለቀሰ፥ ሲሄድም፦ ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ በአንተ ፋንታ ሞቼ ኖሮ ቢሆን፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 18:33
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህም ነገር በአ​ብ​ር​ሃም ዘንድ ስለ ልጁ እጅግ ችግር ሆነ​በት።


የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም የን​ጉሡ ልብ ወደ አቤ​ሴ​ሎም እን​ዳ​ዘ​ነ​በለ ዐወቀ።


ለኢ​ዮ​አብ፥ “ንጉሡ ስለ አቤ​ሴ​ሎም ያዝ​ናል፤ ያለ​ቅ​ሳ​ልም” ብለው ነገ​ሩት።


ንጉ​ሡም ፊቱን ሸፈነ፤ ንጉ​ሡም በታ​ላቅ ድምፅ፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ” እያለ ይጮህ ነበር።


ተራ​ሮ​ችን ከው​ስ​ጣ​ቸው የሚ​ያ​ጠ​ጣ​ቸው፤ ከሥ​ራህ ፍሬ ምድር ትጠ​ግ​ባ​ለች።


አሁ​ንም ይህን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ትላ​ቸው እን​ደ​ሆነ ይቅር በላ​ቸው፤ ያለ​ዚያ ግን ከጻ​ፍ​ኸው መጽ​ሐፍ ደም​ስ​ሰኝ” አለ።


ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናታል።


አላዋቂ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፥ ለወለደችውም ኀዘን ነው።


በሥጋ ዘመ​ዶ​ችና ወን​ድ​ሞች ስለ​ሚ​ሆኑ እኔ ከክ​ር​ስ​ቶስ እለይ ዘንድ እጸ​ል​ያ​ለሁ።


ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፤ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች