Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 18:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ንጉ​ሡም ኩሲን፥ “ብላ​ቴ​ናው አቤ​ሴ​ሎም ደኅና ነውን?” አለው። ኩሲም፥ “የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ጠላ​ቶች፥ በክ​ፉም የተ​ነ​ሡ​ብህ ሁሉ እን​ደ​ዚያ ብላ​ቴና ይሁኑ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን፣ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢትዮጵያዊውም፣ “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶችና ሊጐዱህ የሚነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ወጣት ይሁኑ” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን፥ “ወጣቱ አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢትዮጵያዊውም፥ “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶችና ሊጐዱህ የሚነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ወጣት ይሁኑ” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ንጉሡም “ወጣቱ አቤሴሎም ምንም ጒዳት አልደረሰበትምን?” ሲል ጠየቀ። አገልጋዩም “ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ላይ የደረሰ ነገር በጠላቶችህና በአንተ ላይ በዐመፁት ሁሉ ላይ ይድረስ!” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ንጉሡም ኵሲን፦ ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን? አለው። ኵሲም፦ የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶች፥ በክፉም የተነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ብላቴና ይሁኑ ብሎ መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 18:32
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮ​አ​ብም ኩሲን፥ “ሂድ፤ ያየ​ኸ​ው​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ንገር” አለው። ኩሲም ለኢ​ዮ​አብ ሰግዶ ወጣ።


ንጉ​ሡም፥ “ብላ​ቴ​ናው አቤ​ሴ​ሎም ደኅና ነውን?” አለ። አኪ​ማ​ሖ​ስም፥ “ኢዮ​አብ እኔን ባሪ​ያ​ህ​ንና የን​ጉ​ሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ብዙ ሰዎ​ችን አይ​ቻ​ለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


አቤቱ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ እን​ዲሁ ይጥፉ፤ ወዳ​ጆ​ችህ ግን ፀሐይ በኀ​ይሉ በወጣ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ሆን፤ እን​ዲሁ ይሁኑ። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።


አሁ​ንም ጌታዬ ሆይ! ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ወደ ንጹሕ ደም እን​ዳ​ት​ገ​ባና፥ እጅ​ህን እን​ድ​ታ​ድን የከ​ለ​ከ​ለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ች​ህና በጌ​ታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች