Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 8:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ኤዶ​ም​ያስ ግን ለይ​ሁዳ እን​ዳ​ይ​ገ​ብር እስከ ዛሬ ድረስ በይ​ሁዳ ላይ ሸፈተ። በዚ​ያም ዘመን ደግሞ የሎ​ምና ሰዎች ሸፈቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው፤ ልብናም በዚሁ ጊዜ ዐምፆ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ኤዶም ከይሁዳ ተገዢነት ነጻ ወጣች፤ በዚያኑ ጊዜም የልብና ከተማ ዐመፀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ኤዶም ከይሁዳ ተገዢነት ነጻ ወጣች፤ በዚያኑ ጊዜም የልብና ከተማ ዐመፀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ኤዶምያስ ግን ለይሁዳ እንዳይገብር እስከ ዛሬ ድረስ ሸፈተ። በዚያም ዘመን ደግሞ ልብና ሸፈተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 8:22
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሰ​ይ​ፍ​ህም ትኖ​ራ​ለህ፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ትገ​ዛ​ለህ፤ ነገር ግን ቀን​በ​ሩን ከአ​ን​ገ​ትህ ልት​ጥል ብት​ወ​ድድ ከእ​ርሱ ጋር ተስ​ማማ።”


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከለ​ኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበ​ርና ራፋ​ስ​ቂስ ተመ​ልሶ በሎ​ምና ሲዋጋ አገ​ኘው።


በእ​ር​ሱም ዘመን የኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎች ሸፍ​ተው የይ​ሁዳ ሰዎ​ችን ከዱ​አ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ንጉሥ አነ​ገሡ።


የተ​ረ​ፈ​ውም የኢ​ዮ​ራም ነገር ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


ኤዶ​ም​ያስ ግን በይ​ሁዳ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፀ፤ በዚ​ያም ዘመን ልብና ደግሞ በእ​ርሱ ላይ ዐመፀ፤ የአ​ባ​ቶ​ቹን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትቶ ነበ​ርና።


የኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎች ዳግ​መኛ መጥ​ተው፥ ይሁ​ዳ​ንም መት​ተው ብዙ ምር​ኮኛ ወስ​ደው ነበ​ርና።


ሴዴ​ቅ​ያስ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የል​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።


ለካ​ህ​ኑም ለአ​ሮን ልጆች እነ​ዚ​ህን ሰጡ፤ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ኬብ​ሮ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሌም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች