Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 8:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በአ​ክ​ዓብ ልጅ በኢ​ዮ​ራም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ኢዮ​ራም በይ​ሁዳ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በዐምስተኛው ዓመት፣ የኢዮሣፍጥ ልጅ ይሆራም በይሁዳ ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ ላይ ነገሠ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ ላይ ነገሠ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በእስራኤልም ንጉሥ በአክዓብ ልጅ በኢዮራም በአምስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 8:16
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ አም​ስት ዓመት ጎበዝ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ አም​ስት ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ዓዙባ የተ​ባ​ለች የሴ​ሜይ ልጅ ነበ​ረች።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ጋር ታረቀ።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ ኢዮ​ራም ነገሠ።


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ክ​ዓብ ልጅ አካ​ዝ​ያስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ሁለት ዓመት ነገሠ።


ኤል​ያ​ስም እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሞተ።


የን​ጉሡ የኢ​ዮ​ራም ልጅ የአ​ካ​ዝ​ያስ እኅት ኢዮ​ሳ​ቡ​ሄም የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ስን ከተ​ገ​ደ​ሉት ከን​ጉሡ ልጆች መካ​ከል ሰርቃ ወሰ​ደ​ችው፤ እር​ሱ​ንና ሞግ​ዚ​ቱ​ንም ወደ እል​ፍኝ ወሰ​ደች፤ ከጎ​ቶ​ል​ያም ሸሸ​ገ​ችው፤ አል​ገ​ደ​ሉ​ት​ምም።


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ክ​ዓብ ልጅ ኢዮ​ራም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ ዐሥራ ሁለ​ትም ዓመት ነገሠ።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በአ​ክ​ዓብ ልጅ በኢ​ዮ​ራም በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የነ​በ​ሩት ታና​ሹን ልጁን አካ​ዝ​ያ​ስን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት። የመ​ጣ​ባ​ቸው የዓ​ረ​ብና የአ​ሊ​ማ​ዞን የሽ​ፍ​ቶች ጭፍራ የእ​ር​ሱን ታላ​ቆች ወን​ድ​ሞች ገድ​ለ​ዋ​ቸው ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች