Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሂድ፥ መዳ​ንስ ትድ​ና​ለህ በለው፤ ነገር ግን እን​ዲ​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ይ​ቶ​ኛል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ኤልሳዕም፣ “ሂድና፣ ‘መዳኑንስ በርግጥ ትድናለህ’ በለው፤ ነገር ግን እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጾልኛል” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ኤልሳዕም “ቤንሀዳድ እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤ አንተ ግን ትድናለህ ብለህ ንገረው” አለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኤልሳዕም “ቤንሀዳድ እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤ አንተ ግን ትድናለህ ብለህ ንገረው” አለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ኤልሳዕም “ሂድ፤ ‘መዳንስ ትድናለህ፤’ በለው፤ ነገር ግን እንዲሞት እግዚአብሔር አሳይቶኛል፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 8:10
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን መል​ካ​ም​ንና ክፉን ከሚ​ያ​ሳ​የ​ውና ከሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀው ዛፍ አት​ብላ፤ ከእ​ርሱ በበ​ላህ ቀን ሞትን ትሞ​ታ​ለ​ህና።”


ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሁሉ ገል​ጦ​ል​ሃ​ልና ከአ​ንተ ይልቅ ብል​ህና ዐዋቂ ሰው የለም።


ወደ ንጉ​ሡም ደረሰ። ንጉ​ሡም፥ “ሚክ​ያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ እን​ሂ​ድን? ወይስ እን​ቅር?” አለው። እር​ሱም፥ “ውጣና ተከ​ና​ወን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በን​ጉሡ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታል” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ለምን ላክህ? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም” አለው።


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በላ​ቸው” አለው። ኤል​ያ​ስም ሄደ፤ እን​ዲ​ሁም ነገ​ራ​ቸው።


ትወጣ ዘንድ እንቢ ብትል ግን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​የኝ ቃል ይህ ነው።


ያየ​ሁ​ትም ራእይ ከእኔ ወጣ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያሳ​የ​ኝን ነገር ሁሉ ለም​ር​ኮ​ኞች ተና​ገ​ርሁ።


በአ​ራጣ ቢያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ቢወ​ስድ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሰው በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም፤ ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ይሞ​ታል፤ ደሙም በላዩ ይሆ​ናል።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያ​ዎቹ ለነ​ቢ​ያት ያል​ገ​ለ​ጠ​ው​ንና ያል​ነ​ገ​ረ​ውን ምንም አያ​ደ​ር​ግ​ምና።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ከም​ሥ​ራቅ አን​በጣ ይመ​ጣል፤ አን​ዱም ኵብ​ኵባ ንጉሡ ጎግ ነበረ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ፍ​ረድ በቃሉ እሳ​ትን ጠራ፤ እር​ስ​ዋም ታላ​ቁን ቀላ​ይና ምድ​ርን በላች።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም አንድ ሰው በቱ​ንቢ በተ​ሠራ ቅጥር ላይ ቆሞ ነበር፤ በእ​ጁም ቱንቢ ነበር።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም የቃ​ር​ሚያ ፍሬ የሞ​ላ​በት ዕን​ቅብ ነበረ።


እግዚአብሔርም አራት ጠራቢዎች አሳየኝ።


በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውሃ ወንዝ አሳየኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች