Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 6:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በሰ​ማ​ር​ያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነ​ሆም፥ የአ​ህያ ራስ በኀ​ምሳ ብር፥ የድ​ርጎ አንድ አራ​ተኛ የሚ​ሆን ኵስሐ ርግ​ብም በአ​ም​ስት ብር እስ​ኪ​ሽጥ ድረስ ከበ​ቡ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከተማዪቱን እንደ ከበባትም የአንድ አህያ ጭንቅላት በሰማንያ ሰቅል ብር፣ የጎሞር አንድ ስምንተኛ የርግብ ኵስ በዐምስት ሰቅል ብር እስኪሸጥ ድረስ ታላቅ ራብ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከበባውም የምግብን እጥረትና ብርቱ ራብ ከማስከተሉ የተነሣ፥ የአንድ አህያ ራስ ዋጋ እስከ ሰማኒያ ጥሬ ብር፥ ሁለት መቶ ግራም የሚያኽል የርግብ ኩስ ዋጋ ደግሞ አምስት ጥሬ ብር ማውጣት ጀመረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከበባውም የምግብን እጥረትና ብርቱ ራብ ከማስከተሉ የተነሣ፥ የአንድ አህያ ራስ ዋጋ እስከ ሰማኒያ ጥሬ ብር፥ ሁለት መቶ ግራም የሚያኽል የርግብ ኩስ ዋጋ ደግሞ አምስት ጥሬ ብር ማውጣት ጀመረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በሰማርያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነሆም፥ የአህያ ራስ በአምሳ ብር፥ የርግብም ኩስ የጎሞር ስምንተኛ የሚሆን በአምስት ብር እስኪሸጥ ድረስ ከበቡአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 6:25
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ተራበ፤ ሕዝ​ቡም ስለ እህል ወደ ፈር​ዖን ጮኸ፤ ፈር​ዖ​ንም የግ​ብፅ ሰዎ​ችን ሁሉ፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፤ እርሱ ያላ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።


ኤል​ያ​ስም ለአ​ክ​ዓብ ይገ​ለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ራብ ጸንቶ ነበር።


በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ራብ ጸንቶ ነበ​ርና ለሀ​ገሩ ሰዎች እህል ታጣ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በቅ​ጥር ላይ ሲመ​ላ​ለስ አን​ዲት ሴት፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ርዳኝ” ብላ ወደ እርሱ ጮኸች።


ንጉ​ሡም በሌ​ሊት ተነ​ሥቶ ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ያደ​ረ​ጉ​ብ​ንን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ተራ​ብን ያው​ቃሉ፤ ስለ​ዚህ፦ ከከ​ተ​ማ​ይቱ በወጡ ጊዜ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው እን​ይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለን፤ ወደ ከተ​ማም እን​ገ​ባ​ለን ብለው በሜዳ ይሸ​ሸጉ ዘንድ ከሰ​ፈሩ ወጥ​ተ​ዋል” አላ​ቸው።


ወደ ከተማ ብን​ገባ ራብ በከ​ተማ አለና፥ በዚያ እን​ሞ​ታ​ለን፤ በዚ​ህም ብን​ቀ​መጥ እን​ሞ​ታ​ለን። እን​ግ​ዲህ ኑ፥ ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር እን​ሂድ፤ በሕ​ይ​ወት ቢያ​ኖ​ሩን እን​ኖ​ራ​ለን፤ ቢገ​ድ​ሉ​ንም እን​ሞ​ታ​ለን” ተባ​ባሉ።


ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ በሰ​ይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተ​ማም ብገባ፥ እነሆ በራብ የከሱ አሉ፤ ነቢ​ዩና ካህኑ ወደ​ማ​ያ​ው​ቋት ሀገር ሄደ​ዋ​ልና።”


አሕ​ዛ​ብም መጥ​ተው ይህ​ችን ሀገር ያዟት፤ ይህ​ችም ከተማ ከረ​ኃ​ቡና ከጦሩ የተ​ነሣ በወ​ጓት በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች እጅ ወደ​ቀች፤ እንደ ተና​ገ​ር​ኸ​ውም ሆነ።


በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ወር በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ራብ ጸንቶ ነበር፤ ለሀ​ገ​ሩም ሰዎች እን​ጀራ ታጣ።


ይህም እን​ጀ​ራ​ንና ውኃን እን​ዲ​ያጡ፥ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲ​ገ​ዳ​ደሉ፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እን​ዲ​ጠፉ ነው።


በእ​ህል ረሃብ ባስ​ጨ​ነ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ ዐሥር ሴቶች እን​ጀራ በአ​ንድ ምጣድ ይጋ​ግ​ራሉ፤ በሚ​ዛ​ንም መዝ​ነው እን​ጀ​ራ​ች​ሁን ይመ​ል​ሱ​ላ​ች​ኋል፤ በበ​ላ​ች​ሁም ጊዜ አት​ጠ​ግ​ቡም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች