Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አሁ​ንም ባለ በገና አም​ጡ​ልኝ” አለ። ባለ በገ​ና​ውም በደ​ረ​ደረ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አሁንም ባለበገና አምጡልኝ።” ታዲያ ባለበገናው በሚደረድርበት ጊዜ፣ የእግዚአብሔር እጅ በኤልሳዕ ላይ መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አሁንም በገና የሚደረድር ሰው አምጡልኝ” አለ። ባለ በገናውም በሚደረድርበት ጊዜ የእግዚአብሔር ኃይል በኤልሳዕ ላይ ወርዶ እንዲህ አለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አሁንም በገና የሚደረድር ሰው አምጡልኝ” አለ። ባለ በገናውም በሚደረድርበት ጊዜ የእግዚአብሔር ኀይል በኤልሳዕ ላይ ወርዶ እንዲህ አለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አሁንም ባለ በገና አምጡልኝ፤” አለ። ባለ በገናውም በደረደረ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅ መጣችበት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 3:15
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በኤ​ል​ያስ ላይ ነበ​ረች፤ ወገ​ቡ​ንም ታጥቆ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል እስ​ኪ​ገባ ድረስ በአ​ክ​ዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድ​ጓድ ቈፍሩ።


በላይ ያለ​ውን ሰማ​ይን ምድ​ር​ንም በሕ​ዝቡ ለመ​ፍ​ረድ ይጠ​ራል፥


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሀገር በኮ​ቦር ወንዝ ላይ ወደ ቡዝ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝ​ቅ​ኤል መጣ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በዚያ በእኔ ላይ ሆነች፤


መን​ፈ​ስም አን​ሥቶ ወሰ​ደኝ፤ እኔም በም​ሬ​ትና በመ​ን​ፈሴ ሙቀት ሄድሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ በር​ትታ ነበር።


በዚ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበ​ረች፤ እር​ሱም፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሜዳ ሂድ፤ በዚ​ያም እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለኝ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን በቤቴ ተቀ​ምጬ ሳለሁ፥ የይ​ሁ​ዳም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በፊቴ ተቀ​ም​ጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በላዬ መጣ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ወደ ጌታም ተመ​ል​ሰው ያመኑ ሰዎች ቍጥ​ራ​ቸው በዛ።


ከዚ​ያም በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ ወዳ​ለ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኮረ​ብታ ትመ​ጣ​ለህ፤ በዚ​ያም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ናሴብ አለ፤ ወደ​ዚ​ያም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በደ​ረ​ስህ ጊዜ በገ​ናና ከበሮ፥ እም​ቢ​ል​ታና መሰ​ንቆ ይዘው ትን​ቢት እየ​ተ​ና​ገሩ ከኰ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ የሚ​ወ​ርዱ የነ​ቢ​ያ​ትን ጉባኤ ታገ​ኛ​ለህ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በፊ​ትህ ይና​ገሩ፤ በበ​ገና የሚ​ዘ​ምር ሰውም ለጌ​ታ​ቸው ይፈ​ል​ጉ​ለት፤ ክፉ መን​ፈ​ስም በመ​ጣ​ብህ ጊዜ በገ​ና​ውን ሲመታ አንተ ደኅና ትሆ​ና​ለህ፤ እር​ሱም ያሳ​ር​ፍ​ሃል” አሉት።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ያ ክፉ መን​ፈስ በሳ​ኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦ​ል​ንም ደስ ያሰ​ኘው፥ ያሳ​ር​ፈ​ውም ነበር፥ ክፉው መን​ፈ​ስም ከእ​ርሱ ይርቅ ነበር።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሳኦ​ልን ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤ​ቱም ውስጥ ትን​ቢት ተና​ገረ። ዳዊ​ትም በየ​ቀኑ ያደ​ርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦ​ልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች