Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 24:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የዮ​አ​ኪ​ንን አጎት ማታ​ን​ያን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ሴዴ​ቅ​ያስ ብሎ ለወ​ጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከዚያም የዮአኪንን አጎት ማታንያን በምትኩ አነገሠው፤ ስሙንም ሴዴቅያስ ብሎ ለወጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ናቡከደነፆር በኢኮንያን ምትክ ማታንያ ተብሎ የሚጠራውን የዮአኪንን አጐት በይሁዳ አነገሠ፤ ስሙንም በመለወጥ ሴዴቅያስ ብሎ ጠራው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ናቡከደነፆር በኢኮንያን ምትክ ማታንያ ተብሎ የሚጠራውን የዮአኪንን አጐት በይሁዳ አነገሠ፤ ስሙንም በመለወጥ ሴዴቅያስ ብሎ ጠራው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የባቢሎንም ንጉሥ የዮአኪንን አጎት ማታንያን በእርሱ ፋንታ አነገሠ፤ ስሙንም ሴዴቅያስ ብሎ ለወጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 24:17
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈር​ዖን ኒካ​ዑም የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኤል​ያ​ቄ​ምን በአ​ባቱ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ኢዮ​አ​ቄም ብሎ ለወ​ጠው። ዮአ​ክ​ስ​ንም ወስዶ ወደ ግብፅ አፈ​ለ​ሰው፤ በዚ​ያም ሞተ።


የግ​ብ​ፅም ንጉሥ ፈር​ዖን ኒካዑ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኤል​ያ​ቄ​ምን በአ​ባቱ ፋንታ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ኢዮ​አ​ቄም ብሎ ለወጠ፤ ፈር​ዖን ኒካ​ዑም ወን​ድ​ሙን ኢዮ​አ​ክ​ስን ይዞ ወደ ግብፅ ወሰ​ደው። በዚ​ያም ሞተ። 4 ‘ሀ’ ወር​ቅ​ንና ብርን ለፈ​ር​ዖን ሰጠ። በዚ​ያን ጊዜም ምድር በፈ​ር​ዖን ትእ​ዛዝ ብር መገ​በ​ሯን ጀመ​ረች። 4 ‘ለ’ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም እን​ደ​ሚ​ች​ለው ለፈ​ር​ዖን ኒካዑ እን​ዲ​ገ​ብር ከሀ​ገ​ሪቱ ሕዝብ ወር​ቅ​ንና ብርን ጠየቀ።


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ እስከ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተማ​ረ​ከ​ች​በት እስከ አም​ስ​ተ​ኛው ወር ድረስ መጣ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ የመ​ል​ክ​ያን ልጅ ጳስ​ኮ​ር​ንና የካ​ህ​ኑን የመ​ዕ​ሴ​ይን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ኤር​ም​ያስ በላከ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እን​ዲ​ህም አለ፦


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በይ​ሁዳ ያነ​ገ​ሠው የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ በኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ በኢ​ኮ​ን​ያን ፋንታ ነገሠ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመተ መን​ግ​ሥት ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።


ሴዴ​ቅ​ያስ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የል​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።


ከመ​ን​ግ​ሥ​ትም ዘር ወስዶ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ አማ​ለ​ውም፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ኀያ​ላን ወሰደ፤


“እኔ ሕያው ነኝ! ያነ​ገ​ሠ​ውና መሐ​ላ​ውን የና​ቀ​በት፥ ቃል ኪዳ​ኑ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​በት ንጉሥ በሚ​ኖ​ር​በት ስፍራ ከእ​ርሱ ጋር በባ​ቢ​ሎን መካ​ከል በር​ግጥ ይሞ​ታል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ልጆች ወደ እር​ስዋ መጥ​ተው በመ​ኝ​ታዋ ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኙ፤ በዝ​ሙ​ታ​ቸ​ውም አረ​ከ​ሱ​አት፤ እር​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ረከ​ሰች፤ ነፍ​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ተለ​የች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች