Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 23:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ፈር​ዖን ኒካ​ዑም የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኤል​ያ​ቄ​ምን በአ​ባቱ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ኢዮ​አ​ቄም ብሎ ለወ​ጠው። ዮአ​ክ​ስ​ንም ወስዶ ወደ ግብፅ አፈ​ለ​ሰው፤ በዚ​ያም ሞተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ፈርዖን ኒካዑ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ እግር አነገሠው፤ ኤልያቄም የተባለ ስሙንም ለውጦ ኢዮአቄም አለው። ነገር ግን ኢዮአካዝን በምርኮ ወደ ግብጽ ወሰደው፤ እርሱም በዚያ ሞተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ፈርዖን ኒካዑም የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ አነገሠ፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው። ኢዮአካዝንም ወስዶ ወደ ግብጽ አፈለሰው፤ በዚያም ሞተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 23:34
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ስም “እስ​ፍ​ን​ቶ​ፎ​ኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ የም​ት​ሆን አስ​ኔ​ት​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።


በእ​ር​ሱም ዘመን የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ኒካዑ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ሊጋ​ጠም ወደ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉ​ሡም ኢዮ​ስ​ያስ ከእ​ርሱ ጋር ሊጋ​ጠም ወጣ፤ ፈር​ዖ​ንም በተ​ገ​ና​ኘው ጊዜ በመ​ጊዶ ገደ​ለው።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የዮ​አ​ኪ​ንን አጎት ማታ​ን​ያን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ሴዴ​ቅ​ያስ ብሎ ለወ​ጠው።


የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስም ልጆች፤ በኵሩ ዮሐ​ናን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ኢዮ​አ​ቄም፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ አራ​ተ​ኛ​ውም ሰሎም።


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ እስከ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተማ​ረ​ከ​ች​በት እስከ አም​ስ​ተ​ኛው ወር ድረስ መጣ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እን​ዲህ ሲል፦


በሰ​ሜ​ንም በኩል ወደ ቤተ ራባ ጀርባ ያል​ፋል። በመ​ስ​ዕም ወደ ባሕር መን​ገድ ይወ​ር​ዳል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች