Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 23:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ዮአ​ክ​ስም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ወር ነገሠ። እና​ቱም አሚ​ጣል ትባል ነበር፥ እር​ስ​ዋም የሎ​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ኢዮአካዝ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ሦስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ወር ገዛ። እናቱ አሚጣል ትባላለች፤ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ኢዮአካዝ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሀያ ሦስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ኢዮአካዝ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ ሦስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ኢዮአካዝም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ ሦስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። እናቱም አሚጣል ትባል ነበር፤ እርስዋም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 23:31
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የሎ​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።


የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስም ልጆች፤ በኵሩ ዮሐ​ናን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ኢዮ​አ​ቄም፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ አራ​ተ​ኛ​ውም ሰሎም።


የሀ​ገ​ሩም ሰዎች የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ክ​ስን ወስ​ደው በአ​ባቱ ፋንታ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አነ​ገ​ሡት።


በአ​ባቱ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ፋንታ ስለ ነገ​ሠው፥ ከዚ​ህም ስፍራ ስለ ወጣ​ውና ስለ​ማ​ይ​መ​ለ​ሰው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ፥ ስለ ሳሌም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦


ሴዴ​ቅ​ያስ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የል​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች