Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 23:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ነገር ግን ምናሴ ስላ​ስ​ቈ​ጣው ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በይ​ሁዳ ላይ ከነ​ደ​ደው ከታ​ላቁ ቍጣው ትኵ​ሳት አል​ተ​መ​ለ​ሰም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ይህም ሆኖ እንኳ ለቍጣ እንዲነሣሣ ምናሴ ካደረጋቸው ነገሮች ሁሉ የተነሣ፣ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ከነደደው ከአስፈሪው ቍጣው ገና አልበረደም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ነገር ግን ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው አስፈሪ የእግዚአብሔር ቁጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ነገር ግን ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው አስፈሪ የእግዚአብሔር ቊጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ነገር ግን ምናሴ ስላስቈጣው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ከነደደው ከታላቁ ቍጣው ትኵሳት አልተመለሰም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 23:26
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“አባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ር​ስዋ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚ​ህ​ችን መጽ​ሐፍ ቃል ስላ​ል​ሰሙ በላ​ያ​ችን የነ​ደደ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳ​ችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁ​ዳም ሁሉ ስለ​ዚ​ችም ስለ​ተ​ገ​ኘ​ችው መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን አደጋ ጣዮች፥ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደ​ደ​በት፤ በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያጠ​ፉት ዘንድ በይ​ሁዳ ላይ ሰደ​ዳ​ቸው።


ከፊቱ አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ ይህ ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


ምና​ሴም ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ከፊቱ ያር​ቀው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ሆነ፤


ጻድ​ቁ​ንም ስለ ገደለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራራ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።


ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ፥ ኢዮ​ስ​ያ​ስም ቤተ መቅ​ደ​ሱን ካሰ​ናዳ በኋላ፥ የግ​ብጽ ንጉሥ ፈር​ዖን ኒካዑ በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ይዋጋ ዘንድ ወጣ፤ ኢዮ​ስ​ያ​ስም ሊጋ​ጠ​መው ወጣ።


እነ​ርሱ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በሕ​ዝቡ ላይ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ፥ ፈው​ስም እስ​ከ​ማ​ይ​ገ​ኝ​ላ​ቸው ድረስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክ​ተ​ኞች ይሳ​ለቁ፥ ቃሉ​ንም ያቃ​ልሉ፥ በነ​ቢ​ያ​ቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በጉ​ባ​ኤው ፋንታ ሁሉ ይቁሙ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር የአ​ም​ላ​ካ​ችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመ​ለስ ዘንድ እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገ​ቡት በከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን ያሉት ሁሉ በተ​ቀ​ጠ​ረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የከ​ተ​ማው ሁሉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ፈራ​ጆች ይምጡ።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ የል​ቡን ዐሳብ ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ አይ​መ​ለ​ስም፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን ያው​ቁ​ታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች