Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 20:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያ​ስም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጥቶ፥ “እነ​ዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወ​ዴ​ትስ ወደ አንተ መጡ?” አለው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ከሩቅ ሀገር ከባ​ቢ​ሎን ወደ እኔ መጡ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ መጥቶ፣ “እነዚያ ሰዎች ምን አሉህ? ወደ አንተ ዘንድ የመጡትስ ከየት ነው?” አለው። ሕዝቅያስም መልሶ፣ “የመጡት ከሩቅ አገር ከባቢሎን ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በዚያን ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ፥ “እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ?” ብሎ ጠየቀው። ሕዝቅያስም “እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በዚያን ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ፥ “እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ?” ብሎ ጠየቀው። ሕዝቅያስም “እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡልህ?” አለው። ሕዝቅያስም “ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 20:14
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በእ​ነ​ርሱ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱ​ንም ሁሉ፥ ብሩ​ንና ወር​ቁ​ንም፥ ሽቱ​ው​ንና የከ​በ​ረ​ው​ንም ዘይት፥ መሣ​ሪ​ያም ያለ​በ​ትን ቤት በቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም የተ​ገ​ኘ​ውን ሁሉ አሳ​ያ​ቸው፤ በቤ​ቱና በግ​ዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝ​ቅ​ያስ ያላ​ሳ​ያ​ቸው የለም።


እር​ሱም፥ “ምን አዩ?” አለው ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “በቤቴ ያለ​ውን ሁሉ አይ​ተ​ዋል፤ በቤተ መዛ​ግ​ብ​ቴም ካለው ያላ​ሳ​የ​ኋ​ቸው የለም” አለው።


አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦ “አንተ ተስ​ፋዬ ነህ፥ በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር አንተ ዕድል ፋን​ታዬ ነህ” አልሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና የቍ​ጣው ሠራ​ዊት ዓለ​ምን ያጠ​ፉ​አት ዘንድ ከሩቅ ሀገር ከሰ​ማይ ዳርቻ ይመ​ጣሉ።


እነ​ር​ሱም የባ​ቢ​ሎን ልጆች፥ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አሦ​ራ​ው​ያን ሁሉ፥ መልከ መል​ካ​ሞች ጐበ​ዛ​ዝት፥ መሳ​ፍ​ን​ትና መኳ​ን​ንት ሁሉ፥ መሳ​ፍ​ን​ትና አማ​ካ​ሪ​ዎች ሁሉ፥ በሦ​ስት ወገን በፈ​ረስ ላይ የተ​ቀ​መጡ ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ በለ​ዓም መጥቶ፥ “እነ​ዚህ በአ​ንተ ዘንድ ያሉ ሰዎች እነ​ማን ናቸው?” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንስር እን​ደ​ሚ​በ​ርር ከሩቅ ሀገር፥ ከም​ድር ዳር ቋን​ቋ​ቸ​ውን የማ​ት​ሰ​ማ​ውን ሕዝብ፥


ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ጉባኤ ወደ ጌል​ገላ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥ​ተ​ናል፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ” አሉ።


እነ​ር​ሱም አሉት፥ “በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪ​ያ​ዎ​ችህ መጥ​ተ​ናል፤ ዝና​ው​ንም፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች