Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 20:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “ጥላው ዐሥር ደረጃ ቢጨ​ምር ቀላል ነገር ነው፤ እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመ​ለሰ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሕዝቅያስም መልሶ፣ “ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት መሄዱ ቀላል ነገር ነው፤ ይልቁን ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሕዝቅያስም “ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ማድረግ ይቀላል፤ ስለዚህ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አድርግልኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሕዝቅያስም “ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ማድረግ ይቀላል፤ ስለዚህ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አድርግልኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሕዝቅያስም “ጥላው ዐሥር ደረጃ ቢጨምር ቀላል ነገር ነው፤ እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 20:10
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤል​ያ​ስም፥ “አስ​ቸ​ጋሪ ነገር ለም​ነ​ሃል፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ዘንድ በተ​ወ​ሰ​ድሁ ጊዜ ብታ​የኝ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ አለ​ዚያ ግን አይ​ሆ​ን​ል​ህም” አለው።


ነቢ​ዩም ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ ጥላ​ውም ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመ​ለሰ።


ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ፈ​ጽ​መው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክቱ ይህ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይሂ​ድን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላው ይመ​ለስ?” አለ።


ይህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ቀላል ነገር ነውና፤ ደግ​ሞም ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።


እር​ሱም፥ “የያ​ዕ​ቆ​ብን ነገ​ዶች እን​ደ​ገና እን​ድ​ታ​ስ​ነሣ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​በ​ተ​ኑ​ትን ወደ አባ​ቶች ቃል ኪዳን እን​ድ​ት​መ​ልስ ባር​ያዬ ትሆን ዘንድ ለአ​ንተ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና፥ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድ​ኀ​ኒት ትሆን ዘንድ ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ” ይላል።


“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእኔ የሚ​ያ​ምን እኔ የም​ሠ​ራ​ውን ሥራ እር​ሱም ይሠ​ራል፤ ከዚ​ያም የሚ​በ​ልጥ ይሠ​ራል፤ እኔ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና።


ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እጅ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እርሱ በገ​ባ​ዖን እነ​ር​ሱን ባጠ​ፋ​በት፥ እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በጠ​ፉ​በት ቀን ኢያሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ተነ​ጋ​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “በገ​ባ​ዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፤ በኢ​ሎ​ንም ሸለቆ ጨረቃ፤”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ጠፋ ድረስ ፀሐ​ይና ጨረቃ በየ​ቦ​ታ​ቸው ቆሙ። ይህም እነሆ በዚህ መጽ​ሐፍ በጊ​ዜው ተጻፈ። ፀሐ​ይም በሰ​ማይ መካ​ከል ቆመች፤ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል አል​ጠ​ለ​ቀ​ችም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች