Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 19:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እር​ሱም፥ “የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንጉሥ ቲር​ሐቅ ሊወ​ጋህ መጥ​ቶ​አል” የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ተመ​ልሶ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እን​ዲህ ሲል፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ደግሞም ሰናክሬም፣ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋው መምጣቱን ሰማ፤ ይህንም እንደ ሰማ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞች ላከ፤ እንዲህም አለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እርሱም “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋህ መጥቶአል፤” የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ደግሞ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን እንዲህ ሲል ላከ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 19:9
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አክ​ዓ​ብም ናቡ​ቴን፥ “በቤቴ አቅ​ራ​ቢያ ነውና የአ​ት​ክ​ልት ቦታ አደ​ር​ገው ዘንድ የወ​ይን ቦታ​ህን ስጠኝ፤ ስለ እር​ሱም ከእ​ርሱ የተ​ሻለ የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ወይም ብት​ወ​ድድ ዋጋ​ውን ወርቅ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ረው።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ተር​ታ​ን​ንና ራፌ​ስን ራፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላካ​ቸው። ወጥ​ተ​ውም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ፤ በአ​ጣ​ቢ​ውም እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ዪ​ኛ​ዪቱ ኩሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆሙ።


“ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በአ​ሦር ንጉሥ እጅ አት​ሰ​ጥም ብሎ የም​ት​ታ​መ​ን​በት አም​ላ​ክህ አያ​ታ​ል​ልህ።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከለ​ኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበ​ርና ራፋ​ስ​ቂስ ተመ​ልሶ በሎ​ምና ሲዋጋ አገ​ኘው።


በኢ​ት​ዮ​ጵያ ወን​ዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላ​ቸው መር​ከ​ቦች ላሉ​ባት ምድር ወዮ​ላት!


እር​ሱም፥ “የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንጉሥ ቲር​ሐቅ ሊዋ​ጋህ መጥ​ቶ​አል” የሚል ወሬ ሰማ። በሰ​ማም ጊዜ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እን​ዲህ ሲል፦


ወደ ሳኦ​ልም መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገ​ሩን ወር​ረ​ው​ታ​ልና ፈጥ​ነህ ና” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች