Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 19:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፥ የሰ​ደ​ብ​ኸ​ውስ ማን ነው? ቃል​ህ​ንስ ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ግ​ኸው፥ ዐይ​ን​ህ​ንም ወደ ላይ ያነ​ሣ​ኸው በማን ላይ ነው? በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ለመሆኑ የሰደብኸውና ያቃለልኸው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው? ዐይንህንስ በኵራት ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው እንዴ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የሰደብከውና የተዳፈርከው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? በትዕቢትስ ዐይንህን ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የሰደብከውና የተዳፈርከው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? በትዕቢትስ ዐይንህን ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማንን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግኸው ዐይንህንም ወደ ላይ ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 19:22
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምና​ል​ባት በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ጌታው የአ​ሦር ንጉሥ የላ​ከ​ውን የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስን ቃል ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰማ እን​ደ​ሆነ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሰማው ቃል ይገ​ሥ​ጸው እንደ ሆነ፥ ስለ​ዚህ ለቀ​ረው ቅሬታ ጸልይ።”


ኢሳ​ይ​ያ​ስም አላ​ቸው፥ “ለጌ​ታ​ችሁ እን​ዲህ በሉት፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ሦር ንጉሥ ብላ​ቴ​ኖች ስለ ተሳ​ደ​ቡት፥ ስለ ሰማ​ኸው ቃል አት​ፍራ።


ምል​ክ​ቱ​ንም አና​ው​ቅም፥ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ነቢይ የለም፤ እኛም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አና​ው​ቅም።”


ፈር​ዖ​ንም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እለ​ቅቅ ዘንድ ቃሉን የም​ሰ​ማው እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ው​ቅም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ አል​ለ​ቅ​ቅም” አለ።


አንተ ግን እን​ዳ​ት​ለ​ቃ​ቸው ገና በሕ​ዝቤ ላይ ትታ​በ​ያ​ለህ፤


እርሱ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በኀ​ይሌ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋል ጥበ​ቤም የአ​ሕ​ዛ​ብን ድን​በ​ሮች አር​ቃ​ለሁ፤ ሀብ​ታ​ቸ​ው​ንም እዘ​ር​ፋ​ለሁ፤


“በውኑ መጥ​ረ​ቢያ በሚ​ቈ​ር​ጥ​በት ሰው ላይ ይነ​ሣ​ልን? ወይስ መጋዝ በሚ​ስ​በው ሰው ላይ ይጓ​ደ​ዳ​ልን? ይህም ዘንግ በሚ​መ​ቱ​በት ላይ እንደ መነ​ሣት፥ በት​ርም ዕን​ጨት አይ​ደ​ለ​ሁም እንደ ማለት ነው።”


የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “ብት​ጸ​ጸ​ትና ብታ​ለ​ቅስ ትድ​ና​ለህ፤ የት እን​ዳ​ለ​ህም ታው​ቃ​ለህ፤ በከ​ንቱ ታም​ነ​ሃ​ልና፤ ኀይ​ላ​ች​ሁም ከንቱ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ግን መስ​ማ​ትን እንቢ አላ​ችሁ፤


ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና።


“ምድ​ራ​ቸው በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ በተ​ሠ​ራው በደል የተ​ሞ​ላች ብት​ሆ​ንም፥ እስ​ራ​ኤል መበ​ለት አል​ሆ​ነ​ችም፤ ይሁ​ዳም ከአ​ም​ላኩ ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አል​ራ​ቀም።


ልብ ሁሉ ይማ​ረክ ዘንድ ኅሊ​ናም ለክ​ር​ስ​ቶስ ይገዛ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ የሚ​ታ​በ​የ​ው​ንና ከፍ ከፍ የሚ​ለ​ውን እና​ፈ​ር​ሳ​ለን።


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች