Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 19:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የቤ​ቱ​ንም አዛዥ ኤል​ያ​ቄ​ምን ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳም​ና​ስን የካ​ህ​ና​ቱ​ንም አለ​ቆች ማቅ ለብ​ሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያስ ይሄዱ ዘንድ ላካ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም የቤተ መንግሥቱን አዛዥ ኤልያቄምን፣ ጸሓፊውን ሳምናስንና ከካህናቱ ዋና ዋናዎቹን ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲሄዱ ላካቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ወዲያውም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን ኤልያቄምን፥ የቤተ መንግሥቱን ጸሐፊ ሼብናንና ሽማግሌዎች ካህናትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ራሳቸው ማቅ ለብሰው ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ወዲያውም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን ኤልያቄምን፥ የቤተ መንግሥቱን ጸሐፊ ሼብናንና ሽማግሌዎች ካህናትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ራሳቸው ማቅ ለብሰው ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሐፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 19:2
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ኢዮ​አ​ብ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብ​ሳ​ች​ሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአ​በ​ኔ​ርም ፊት አል​ቅሱ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም ዳዊት ከቃ​ሬ​ዛው በኋላ ሄደ።


በሣ​ጥ​ኑም ውስጥ የተ​ገ​ኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የን​ጉሡ ጸሓ​ፊና የካ​ህ​ናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ ቈጥ​ረው በከ​ረ​ጢት ውስጥ ያኖ​ሩት ነበር።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም ጠሩ፤ የቤ​ቱም አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም ጸሓ​ፊ​ውም ሳም​ናስ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነ​ርሱ ወጡ።


እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ እና​ትም ለማ​ማጥ ኀይል የላ​ትም።


የቀ​ሩ​ትም የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ የዖ​ዝ​ያን ነገ​ሮች በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።


በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት በዖ​ዝ​ያ​ንና በኢ​ዮ​አ​ታም፥ በአ​ካ​ዝና በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን ስለ ይሁ​ዳና ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያየው የአ​ሞጽ ልጅ የኢ​ሳ​ይ​ያስ ራእይ።


ስለ ይሁ​ዳና ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሞፅ ልጅ ወደ ኢሳ​ይ​ያስ የመጣ ቃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸ​ክላ ሠሪ የሠ​ራ​ውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ከካ​ህ​ናት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤


ንጉ​ሡም፥ ይህ​ንም ቃል ሁሉ የሰሙ አገ​ል​ጋ​ዮቹ ሁሉ አል​ደ​ነ​ገ​ጡም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አል​ቀ​ደ​ዱም።


በነቢዩም በኢሳይያስ እንዲህ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ፤


በም​ድረ በዳ የሚ​ጮኽ የአ​ዋጅ ነጋሪ ድምፅ በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ መጽ​ሐፍ ቃል እንደ ተጻፈ፥ እን​ዲህ ሲል፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ፤ ጥር​ጊ​ያ​ው​ንም አስ​ተ​ካ​ክሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች