Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 17:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የአ​ሦ​ርም ንጉሥ፥ “ከዚያ ካመ​ጣ​ኋ​ቸው ካህ​ናት አን​ዱን ውሰዱ፤ ሄዶም በዚያ ይቀ​መጥ፤ የሀ​ገ​ሩ​ንም አም​ላክ ሕግ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው” ብሎ አዘዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ከዚያም የአሦር ንጉሥ፣ “ከሰማርያ ማርካችሁ ካመጣችኋቸው ካህናት አንዱን፣ በዚያው እንዲኖር መልሳችሁ ውሰዱትና የአገሩ አምላክ ምን እንደሚፈልግ ሕዝቡን ያስተምር” ሲል አዘዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ስለዚህም ንጉሠ ነገሥቱ “ማርከን ካመጣናቸው ካህናት አንዱን ወደዚያ ላኩ፤ ወደዚያም ተመልሶ በመሄድ የዚያችን አገር አምላክ ያዘዘውን ሕግ ለሕዝቡ እንዲያስተምራቸው አድርጉ” ሲል አዘዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ስለዚህም ንጉሠ ነገሥቱ “ማርከን ካመጣናቸው ካህናት አንዱን ወደዚያ ላኩ፤ ወደዚያም ተመልሶ በመሄድ የዚያችን አገር አምላክ ያዘዘውን ሕግ ለሕዝቡ እንዲያስተምራቸው አድርጉ” ሲል አዘዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የአሦርም ንጉሥ “ከዚያ ካመጣችኋቸው ካህናት አንዱን ውሰዱ፤ ሄዶም በዚያ ይቀመጥ፤ የአገሩንም አምላክ ወግ ያስተምራቸው፤ ብሎ አዘዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 17:27
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በኮ​ረ​ብ​ቶ​ቹም ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠራ፤ ከሌዊ ልጆች ካይ​ደሉ ከማ​ን​ኛ​ውም ሕዝብ ሁሉ የጣ​ዖት ካህ​ና​ትን ሾመ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ፥ “መሠ​ዊያ ሆይ፥ መሠ​ዊያ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮ​ስ​ያስ የሚ​ባል ልጅ ለዳ​ዊት ቤት ይወ​ለ​ዳል፤ ዕጣ​ንም የሚ​ያ​ጥ​ኑ​ብ​ህን የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹን ካህ​ናት ይሠ​ዋ​ብ​ሃል፤ የሰ​ዎ​ቹ​ንም አጥ​ንት ያቃ​ጥ​ል​ብ​ሃል” ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ጠራ።


ስለ​ዚ​ህም ለአ​ሦር ንጉሥ፥ “ያፈ​ለ​ስ​ኻ​ቸው፥ በሰ​ማ​ር​ያም ከተ​ሞች ያኖ​ር​ኻ​ቸው ሕዝ​ቦች የሀ​ገ​ሩን አም​ላክ ሕግ አላ​ወ​ቁም፤ የሀ​ገ​ሩን አም​ላክ ሕግ አላ​ወ​ቁ​ምና አን​በ​ሶ​ችን ሰድ​ዶ​ባ​ቸ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ እየ​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ነው” ብለው ተና​ገ​ሩት።


ከሰ​ማ​ር​ያም ካፈ​ለ​ሱ​አ​ቸው ካህ​ናት አን​ዱን ወስ​ደው በቤ​ቴል አኖ​ሩት፤ ያም ካህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር።


እርሱ ግን ለኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች፥ ከንቱ ለሆኑ ጣዖ​ታ​ቱም፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ለሠ​ራ​ቸው እን​ቦ​ሶ​ችም ካህ​ና​ትን አቆመ።


አን​ተም ዕዝራ፥ በእ​ጅህ እን​ዳ​ለው እንደ አም​ላ​ክህ ጥበብ መጠን በወ​ንዝ ማዶ ባሉ ሕዝብ ሁሉ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ህን ሕግ በሚ​ያ​ውቁ ሁሉ ላይ ይፈ​ርዱ ዘንድ ጻፎ​ች​ንና ፈራ​ጆ​ችን ሹም፤ የማ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው።


ሚካም፥ “ሌዋዊ ካህን ስለ ሆነ​ልኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካም እን​ዲ​ሠ​ራ​ልኝ አሁን አው​ቃ​ለሁ” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች