Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ምና​ሔ​ምም ብሩን ለአ​ሶር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ በእ​ስ​ራ​ኤል ባለ​ጠ​ጎች ሁሉ ላይ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ላይ አምሳ ሰቅል ብር አስ​ገ​ብሮ አወጣ። የአ​ሶ​ርም ንጉሥ ተመ​ለሰ፤ በሀ​ገ​ሪ​ቱም አል​ተ​ቀ​መ​ጠም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ምናሔም ገንዘቡ እንዲዋጣ ያደረገው ከእስራኤል ሲሆን፣ ይህንም ያደረገው ለአሦር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ እያንዳንዱ ሀብታም ዐምሳ፣ ዐምሳ ሰቅል ብር እንዲያዋጣ በማስገደድ ነበር። ስለዚህ የአሦር ንጉሥ በዚያች አገር አልቈየም፤ ተመልሶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ምናሔም ገንዘቡን የሰበሰበው የእስራኤል ከበርቴዎች እያንዳንዳቸው ኀምሳ ጥሬ ብር አዋጥተው እንዲሰጡ በማስገደድ ነበር። በዚህም ዓይነት ቲግላት ፐሌሴር በሰላም ወደ አገሩ ተመልሶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ምናሔም ገንዘቡን የሰበሰበው የእስራኤል ከበርቴዎች እያንዳንዳቸው ኀምሳ ጥሬ ብር አዋጥተው እንዲሰጡ በማስገደድ ነበር። በዚህም ዐይነት ቲግላት ፐሌሴር በሰላም ወደ አገሩ ተመልሶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ምናሔምም ብሩን ለአሦር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ በእስራኤል ባለ ጠጎች ሁሉ ላይ በእያንዳንዱ ላይ አምሳ ሰቅል ብር አስገብሮ አወጣ። የአሦርም ንጉሥ ተመለሰ፤ በአገሪቱም አልተቀመጠም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 15:20
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቤር​ዜ​ሊም እጅግ ያረጀ የሰ​ማ​ንያ ዓመት ሽማ​ግሌ ነበረ፤ እጅ​ግም ትልቅ ሰው ነበ​ረና ንጉሡ በመ​ና​ሄም ሳለ ይቀ​ል​በው ነበር።


በዘ​መ​ኑም የአ​ሶር ንጉሥ ፎሐ በም​ድ​ሪቱ ላይ ወጣ፤ ምና​ሔ​ምም የፎሐ እጅ ከእ​ርሱ ጋር እን​ዲ​ሆን አንድ ሺህ መክ​ሊት ብር ሰጠው።


የቀ​ረ​ውም የም​ና​ሔም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


ኢዮ​አ​ቄ​ምም ብሩ​ንና ወር​ቁን ለፈ​ር​ዖን ሰጠው፤ እንደ ፈር​ዖ​ንም ትእ​ዛዝ ገን​ዘብ ይሰጥ ዘንድ ምድ​ሩን አስ​ገ​በረ፤ ለፈ​ር​ዖን ኒካ​ዑም ግብር ይሰጥ ዘንድ ከሀ​ገሩ ሕዝብ ሁሉ እንደ ግም​ጋ​ሜው ብርና ወርቅ አስ​ከ​ፈለ።


ከብ​ቶ​ቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመ​ሎች፥ አም​ስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አም​ስት መቶም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት፤ ሥራ​ውም በም​ድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በም​ሥ​ራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።


ለኑኃሚንም ባል የሚዛመደው ከአቤሜሌክ ወገን የሆነ ኃያል ሰው ስሙ ቦዔዝ የተባለ ሰው ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች