Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 8:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በብዙ መከራ ከመ​ፈ​ተ​ና​ቸው የተ​ነሣ ደስ​ታ​ቸው በዝ​ቶ​አ​ልና፤ በድ​ህ​ነ​ታ​ቸው ጥል​ቅ​ነ​ትም የለ​ጋ​ስ​ነ​ታ​ቸው ባለ​ጠ​ግ​ነት በዝ​ታ​ለ​ችና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የደረሰባቸው መከራ ጽኑ ቢሆንም ደስታቸው ግን የላቀ ነበር፤ ድኽነታቸው ብርቱ ቢሆንም ልግስናቸው ግን የበዛ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በብዙ መከራ እየተፈተኑም ቢሆን ደስታቸው እጥፍ ድርብ ነበር፤ የድህነታቸው መጠን ቢበዛም ልግስናቸው የበዛ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እነርሱ በብዙ መከራ ተፈትነዋል፤ ይሁን እንጂ ደስታቸው ታላቅ ነበር፤ በጣም ድኾች ቢሆኑም እንኳ ከፍ ያለ ልግሥና አድርገዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸው ብዛትና የድህነታቸው ጥልቅነት የልግስናቸውን ባለ ጠግነት አብዝቶአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 8:2
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የተባረከች ሰውነት ሁሉ ትጠግባለች፥ ቍጡ ሰው ግን ክፉ ነው።


ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዐይንህ ምቀኛ ናትን?


የሚ​መ​ክ​ርም በመ​ም​ከሩ ይትጋ፤ የሚ​ሰ​ጥም በል​ግ​ስና ይስጥ፤ የሚ​ገ​ዛም በት​ጋት ይግዛ፤ የሚ​መ​ጸ​ው​ትም በደ​ስታ ይመ​ጽ​ውት።


ወይስ በቸ​ር​ነቱ ብዛት በመ​ታ​ገሡ፥ ለአ​ን​ተም እሺ በማ​ለቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ዋቂ ልታ​ደ​ር​ገው ታስ​ባ​ለ​ህን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ቸር​ነቱ አን​ተን ወደ ንስሓ እን​ዲ​መ​ል​ስህ አታ​ው​ቅ​ምን?


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ትና ይቅ​ርታ መመ​ኪ​ያ​ች​ንና የነ​ፃ​ነ​ታ​ችን ምስ​ክር ይህቺ ናትና፥ በሥ​ጋዊ ጥበብ ሳይ​ሆን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይል​ቁ​ንም በእ​ና​ንተ ዘንድ ተመ​ላ​ለ​ስን።


ስለ​ዚ​ህም በሁሉ ትታ​ዘ​ዙኝ እንደ ሆነ፥ ፈቃ​ዳ​ች​ሁን ዐውቅ ዘንድ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።


ኀዘ​ን​ተ​ኞች ስን​ሆን ዘወ​ትር ደስ​ተ​ኞች ነን፤ እንደ ድሆች ስን​ሆን ብዙ​ዎ​ችን እና​በ​ለ​ጽ​ጋ​ለን፤ ምንም የሌ​ለን ስን​ሆን ሁሉ በእ​ጃ​ችን ነው።


ለብዙ ሰዎች ስለ ሰጣ​ች​ሁም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና በም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ ልግ​ስና ሁሉ ባለ​ጸ​ጎች ትሆ​ና​ላ​ችሁ።


ክር​ስ​ቶስ ላስ​ተ​ማ​ራት ትም​ህ​ርት ታዝ​ዛ​ች​ኋ​ልና፥ ሁላ​ች​ሁም ደስ ብሎ​አ​ች​ሁና ተባ​ብ​ራ​ችሁ አወ​ጣ​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና በዚች በሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ ፈተና ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ ርስት አድ​ርጎ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ላይ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና በመ​ካ​ከ​ልህ ድሃ አይ​ኖ​ርም፤


ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤


እናንተ ወንድሞች ሆይ! በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና፤ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበሉ፥ እናንተ ደግሞ ያንን መከራ ከአገራችሁ ሰዎች ተቀብላችኋልና።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


“መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች