Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በዚህ ደግሞ በእ​ና​ንተ ዘንድ ራሳ​ች​ንን የም​ና​መ​ሰ​ግን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እኛ እን​ደ​ም​ን​መ​ካ​ባ​ችሁ፥ እና​ን​ተም በእኛ እን​ድ​ት​መኩ፥ ከልብ ሳይ​ሆን ለሰው ይም​ሰል በሚ​መኩ ሰዎች ዘንድ መልስ እን​ዲ​ሆ​ና​ችሁ ምክ​ን​ያ​ትን እን​ሰ​ጣ​ች​ኋ​ለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ይህን የምለው ራሳችንን በእናንተ ፊት እንደ ገና ለማመስገን ሳይሆን፣ በእኛ እንድትመኩ ዕድል ልሰጣችሁ ነው፤ ይኸውም በውጭ በሚታየው ለሚመኩት እንጂ በልብ ውስጥ ባለው ነገር ለማይመኩ መልስ መስጠት እንድትችሉ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በልብ ሳይሆን በውጫዊ ነገር ለሚመኩ፥ የምትመልሱላቸው መልስ እንዲኖራችሁ፥ በእኛ ልትመኩ ምክንያት ልንሰጣችሁ እንጂ በእናንተ ፊት መልሰን ራሳችንን ለማመስገን ፈልገን አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በልብ ባለው ሳይሆን በሚታየው ለሚመኩ መልስ ለመስጠት እንድትችሉ በእኛ ትመኩ ዘንድ ዕድል እንሰጣችኋለን እንጂ እንደገና እኛ ለእናንተ ራሳችንን አናመሰግንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በመልክ እንጂ በልብ ለማይመኩ የምትመልሱላቸው መልስ እንዲኖራችሁ፥ በእኛ ልትመኩ ምክንያት እንሰጣችኋለን እንጂ ራሳችንን ደግሞ ለእናንተ የምናመሰግን አይደለንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 5:12
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኛ መመ​ኪ​ያ​ችሁ እን​ደ​ሆን፥ እን​ዲሁ እና​ን​ተም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን መመ​ኪ​ያ​ችን እን​ድ​ት​ሆኑ በከ​ፊል እን​ዳ​ወ​ቃ​ችሁ ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውን በአ​ሰ​ቡ​ትና በገ​መ​ገ​ሙት መጠን ራሳ​ቸ​ውን ከሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑት ሰዎች ጋር ራሳ​ች​ንን ልን​ቈ​ጥር፥ ወይም ራሳ​ች​ንን ልና​ስ​ተ​ያይ አን​ደ​ፍ​ርም፤ እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውም የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ትር​ጕ​ሙን አያ​ው​ቁ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያከ​በ​ረው ብቻ ይከ​ብ​ራል እንጂ ራሱን የሚ​ያ​ከ​ብር የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም።


በፊ​ታ​ችሁ ያለ​ውን ተመ​ል​ከቱ፤ ማንም በክ​ር​ስ​ቶስ ያመነ ቢሆን፥ ይህን እንደ ገና በራሱ ይቍ​ጠ​ረው፤ እርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ እኛም እን​ዲሁ ነንና።


እና​ን​ተን ለማ​ነጽ እንጂ፥ እና​ን​ተን ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ጠን ሥል​ጣን እጅግ የተ​መ​ካ​ሁት መመ​ካት ቢኖር አላ​ፍ​ርም።


እነሆ እና​ንተ ስላ​ገ​በ​ራ​ች​ሁኝ በመ​መ​ካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእ​ኔማ በእ​ና​ንተ ዘንድ ልከ​ብ​ርና እና​ን​ተም ምስ​ክ​ሮች ልት​ሆ​ኑኝ ይገ​ባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢም​ንት ብሆ​ንም ዋና​ዎቹ ሐዋ​ር​ያት ሁሉ ከሠ​ሩት ሥራ ያጐ​ደ​ል​ሁ​ባ​ችሁ የለ​ምና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አሁን ደግሞ ራሳ​ች​ንን እያ​መ​ሰ​ገን ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ እን​ጀ​ም​ራ​ለ​ንን? ወይስ እንደ ሌሎች ስለ እኛ ወደ እና​ንተ ደብ​ዳቤ እን​ዲ​ጽ​ፉ​ላ​ችሁ፥ ወይስ እና​ንተ ትጽ​ፉ​ልን ዘንድ የም​ን​ሻው አለን?


ነገር ግን በሁሉ ራሳ​ች​ንን አቅ​ን​ተን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን፤ በብዙ ትዕ​ግ​ሥ​ትና በመ​ከራ፥ በች​ግ​ርና በጭ​ን​ቀት ሁሉ፥


ዳግ​መኛ ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣቴ በእኔ ምክ​ን​ያት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ታ​ገ​ኙት ክብር ይበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች