Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በእ​ስያ መከራ እንደ ተቀ​በ​ልን ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፤ ለሕ​ይ​ወ​ታ​ችን ተስፋ እስ​ክ​ን​ቈ​ርጥ ድረስ ከዐ​ቅ​ማ​ችን በላይ እጅግ መከራ ጸን​ቶ​ብን ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ወንድሞች ሆይ፤ በእስያ ስለ ደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንወድዳለን፤ በሕይወት ለመኖር እንኳ ተስፋ እስከምንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ የሆነ ጽኑ መከራ ደርሶብን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ወንድሞች ሆይ! በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን ብታውቁት እንወዳለን፤ በሕይወታችን ተስፋ እስክመቁረጥ የሚያደርስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ወንድሞች ሆይ! በእስያ ክፍለ ሀገር በነበርንበት ጊዜ የደረሰብንን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ ይህም የደረሰብን መከራ ልንሸከመው ከምንችለው በላይ ወድቆብን ስለ ነበር በሕይወት ለመኖር የነበረን ተስፋ እንኳ ተቋርጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 1:8
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ መን​ፈስ ቅዱስ ስለ​ከ​ለ​ከ​ላ​ቸው ወደ ፍር​ግ​ያና ወደ ገላ​ትያ አው​ራጃ ሄዱ፤


እኛ በተ​ወ​ለ​ድ​ን​በት በጳ​ርቴ፥ በሜድ፥ በኢ​ላ​ሜጤ፥ በሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል፥ በይ​ሁዳ፥ በቀ​ጰ​ዶ​ቅያ፥ በጳ​ን​ጦ​ስና በእ​ስያ፥


ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በሌ​ሎች አሕ​ዛብ እንደ ሆነ በእ​ና​ን​ተም ዋጋ​ዬን አገኝ ዘንድ ሁል​ጊዜ ወደ እና​ንተ ልመጣ እንደ ወደ​ድሁ፥ እስከ ዛሬ ድረ​ስም እንደ ተሳ​ነኝ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።


በውኑ በኤ​ፌ​ሶን ከአ​ውሬ ጋር የታ​ገ​ልሁ ለሰው ብዬ ነውን? ምንስ ይጠ​ቅ​መ​ኛል? ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆነ እን​ግ​ዲህ እን​ብላ እን​ጠጣ፥ ነገም እን​ሞ​ታ​ለን።


ሥራ የሞ​ላ​በት ታላቅ በር ተከ​ፍ​ቶ​ል​ኛ​ልና፤ ነገር ግን ብዙ​ዎች ተቃ​ዋ​ሚ​ዎች አሉ።


እና​ንተ አሁን ጠግ​ባ​ች​ኋል፤ በል​ጽ​ጋ​ች​ኋ​ልም፤ ያለ​እ​ኛም ፈጽ​ማ​ችሁ ነግ​ሣ​ች​ኋል፤ እኛም ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ድ​ን​ነ​ግሥ ብት​ነ​ግሡ አግ​ባብ በሆነ ነበር።


ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ በራ​ሳ​ችን እን​ዳ​ን​ታ​መን በው​ስ​ጣ​ችን ለመ​ሞት ቈር​ጠን ነበር።


እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቁ ስን​ታይ የታ​ወ​ቅን ነን፤ እንደ ሰነ​ፎች ስን​ታ​ይም ልባ​ሞች ነን፤ እንደ ሙታን ስን​ታይ ሕያ​ዋን ነን፤ የተ​ቀ​ጣን ስን​ሆ​ንም አን​ገ​ደ​ልም።


ዳዊ​ትም፥ “እኔ በፊ​ትህ ሞገ​ስን እን​ዳ​ገ​ኘሁ አባ​ትህ በእ​ው​ነት ያው​ቃል፤ እር​ሱም፦ ዮና​ታን እን​ዳ​ይ​ቃ​ወም አይ​ወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስ​ህም እም​ላ​ለሁ፤ እኔ እን​ዳ​ል​ሁት በእ​ኔና በሞት መካ​ከል አንድ ርምጃ ያህል ቀር​ቶ​አል” ብሎ ማለ።


ዳዊ​ትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳ​ኦል እጅ እሞ​ታ​ለሁ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ምድር ከመ​ሸሸ በቀር የሚ​ሻ​ለኝ የለም፤ ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል አው​ራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም ከእጁ እድ​ና​ለሁ” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች