Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 14:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ፥ “እና​ንተ አንድ ወገን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔና ልጄ ዮና​ታ​ንም አንድ ወገን እን​ሆ​ና​ለን” አለ። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን አድ​ርግ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ሳኦልም እስራኤላውያንን ሁሉ፣ “እናንተ በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሰዎቹም፣ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ብለው መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ለእስራኤላውያን ሁሉ፥ “እናንተ በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሰዎቹም፥ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ከዚያም በኋላ ሳኦል “እናንተ ሁላችሁም በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 እስራኤልንም ሁሉ፦ እናንተ በአንድ ወገን ሁኑ፥ እኔና ልጄ ዮናታንም በሌላ ወገን እንሆናለን አለ። ሕዝቡም ሳኦልን ደስ የሚያሰኝህን አድርግ አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 14:40
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የን​ጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖች ንጉ​ሡን፥ “እነሆ፥ ጌታ​ችን ንጉሥ የመ​ረ​ጠ​ውን ሁሉ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉት።


ባል​ዋም ሕል​ቃና፥ “በዐ​ይ​ንሽ ደስ ያሰ​ኘ​ሽን አድ​ርጊ፤ ጡትም እስ​ኪ​ተው ድረስ ተቀ​መጪ፤ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ፍሽ የወ​ጣ​ውን ያጽና” አላት። ሴቲ​ቱም ልጅ​ዋን እያ​ጠ​ባች ጡት እስ​ኪ​ተው ድረስ ተቀ​መ​ጠች።


ሳኦ​ልም፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በሌ​ሊት ተከ​ት​ለን እን​ው​ረድ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ እን​በ​ዝ​ብ​ዛ​ቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አና​ስ​ቀ​ር​ላ​ቸው” አለ። እነ​ር​ሱም፥ “ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን ሁሉ አድ​ርግ” አሉት። ካህ​ኑም፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ቅ​ረብ” አለ።


እስ​ራ​ኤ​ልን የሚ​ያ​ድን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ኀጢ​ኣቱ በልጄ በዮ​ና​ታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለ። ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ አንድ የመ​ለ​ሰ​ለት ሰው አል​ነ​በ​ረም።


ሳኦ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ዛሬ ያል​መ​ለ​ስ​ህ​ልኝ ስለ ምን​ድን ነው? ይህች በደል በእኔ፥ በልጄ በዮ​ና​ታ​ንም እንደ ሆነች አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተና​ገር። ዕጣው ይህን የሚ​ገ​ልጥ ከሆነ ለሕ​ዝ​ብህ ለእ​ስ​ራ​ኤል እው​ነ​ትን ግለጥ፥” አለ። ዕጣም በዮ​ና​ታ​ንና በሳ​ኦል ላይ ወጣ፤ ሕዝ​ቡም ነፃ ወጣ።


ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም፥ “ልብህ ያሰ​ኘ​ህን ሁሉ አድ​ርግ እነሆ፥ ከአ​ንተ ጋር ነኝ፤ እንደ አንተ ልብ የእ​ኔም ልብ እን​ዲሁ ነው” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች