Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ጴጥሮስ 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤” የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ደግሞም፣ “የሚያደናቅፍ፣ የሚጥላቸውም ዐለት ሆነ።” የሚደናቀፉትም ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ የተመደቡት ለዚህ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ደግሞም፦ “ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ የሚጥላቸውም ዓለት ሆነ፤” የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ደግሞም፥ “እነሆ! ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ፤ እነሆ! ሰዎችን አደናቅፎ የሚጥል አለት” ይላል። እነርሱ ቃሉን ባለማመናቸው ይሰናከላሉ፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ጴጥሮስ 2:8
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚ​ህም እኔ ስለ እርሱ ቸኰ​ልሁ፤ በተ​ገ​ሠ​ጽ​ሁም ጊዜ አሰ​ብ​ሁት።


ነገር ግን ኀይ​ሌን እገ​ል​ጥ​ብህ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ላይ ይነ​ገር ዘንድ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁህ።


“እኔ ጥንት የሠ​ራ​ሁ​ትን አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? እኔ በቀ​ድሞ ዘመን እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት፥ አሁ​ንም አሕ​ዛ​ብን በም​ሽ​ጎ​ቻ​ቸው፥ በጽኑ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ያጠፉ ዘንድ አዘ​ዝሁ።


እር​ሱም፥ “በፊቱ፥ መን​ገ​ድን ጥረጉ፤ ከሕ​ዝ​ቤም መን​ገድ ዕን​ቅ​ፋ​ትን አስ​ወ​ግዱ” ይላል።


ብታ​ም​ን​በት ይቀ​ድ​ስ​ሃል፤ እንደ ድን​ጋይ ዕን​ቅ​ፋ​ትም አያ​ደ​ና​ቅ​ፍ​ህም፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ድጥ ዓለ​ትም አይ​ሆ​ን​ብ​ህም፤ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ቤቶች ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ጥ​መ​ድና በአ​ሽ​ክላ ተይ​ዘው ይኖ​ራሉ።


ስም​ዖ​ንም ባረ​ካ​ቸው፤ እና​ቱን ማር​ያ​ም​ንም እን​ዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ለብ​ዙ​ዎች ለመ​ው​ደ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ነ​ሣ​ታ​ቸው፥ ለሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትም ምል​ክት ይሆን ዘንድ የተ​ሠ​የመ ነው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ሉን የሚ​ገ​ል​ጽ​በ​ትን ቅጣ​ቱን ሊያ​ሳይ ቢወድ፥ ትዕ​ግ​ሥ​ቱን ካሳየ በኋላ ለማ​ጥ​ፋት የተ​ዘ​ጋ​ጁ​ትን ቍጣ​ውን የሚ​ገ​ል​ጽ​ባ​ቸ​ውን መላ​እ​ክት ያመ​ጣል።


እኛ ግን የተ​ሰ​ቀ​ለ​ውን ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ሰ​ብ​ካ​ለን፤ ይህም ለአ​ይ​ሁድ ማሰ​ና​ከያ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ስን​ፍና ነው።


የሞት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸው ለሞት፥ የሕ​ይ​ወት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ለሕ​ይ​ወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚ​ገ​ባው ማነው?


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔ ግዝ​ረ​ትን ገና የም​ሰ​ብክ ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ለምን ያሳ​ድ​ዱ​ኛል? እን​ግ​ዲህ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት እን​ዲ​ያው ቀር​ቶ​አል።


እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።


በመጽሐፍ “እነሆ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም፤” ተብሎ ተጽፎአልና።


እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን “አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ


ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም፤ ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።


ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኀጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ብቻውን ንጉሣችንንና ጌታችንንም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች