1 ነገሥት 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እስከዚያም ቀን ድረስ ለእግዚአብሔር ቤት አልተሠራም ነበርና ሕዝቡ በኮረብታ ላይ ይሠዉና ያጥኑ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 በዚያ ጊዜ ለእግዚአብሔር ስም ገና ቤተ መቅደስ ስላልተሠራ፣ ሕዝቡ አሁንም መሥዋዕት የሚያቀርበው በማምለኪያ ኰረብታ ላይ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 በዚያን ጊዜ በጌታ ስም ቤተ መቅደሱ ገና አልተሠራም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ በየኮረብታው መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደሱ ገና አልተሠራም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ በየኮረብታው መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እስከዚያም ቀን ድረስ ለእግዚአብሔር ስም መቅደስ አልተሠራም ነበርና ሕዝቡ በኮረብታ ላይ ባሉት መስገጃዎች ይሠዋ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |