Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ዮሐንስ 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በብርሃን አለሁ የሚል፣ ወንድሙን ግን የሚጠላ አሁንም በጨለማ ውስጥ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በብርሃን አለሁ እያለ ወንድሙን ግን የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ ውስጥ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በብርሃን እኖራለሁ እያለ ወንድሙን የሚጠላ ገና በጨለማ ውስጥ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዮሐንስ 2:9
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም አም​ኖ​ንን ክፉም ሆነ መል​ካም አል​ተ​ና​ገ​ረ​ውም። እኅ​ቱን ትዕ​ማ​ርን ስላ​ስ​ነ​ወ​ራት አቤ​ሴ​ሎም አም​ኖ​ንን ጠል​ቶ​ታ​ልና።


በአ​ን​ድ​ነት ተካ​ክ​ለው ተማ​ክ​ረ​ዋ​ልና፤ በአ​ንተ ላይ ሤራ ቈረጡ፤ ቃል ኪዳ​ንም አደ​ረጉ፤


“ወን​ድ​ም​ህን አት​በ​ድ​ለው፤ በል​ብ​ህም አት​ጥ​ላው፤ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብህ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ት​ነ​ቅ​ፍ​በ​ትን ንገ​ረው፤ ገሥ​ጸ​ውም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ዕዉ​ሮ​ችስ ብት​ሆኑ ኀጢ​ኣት ባል​ሆ​ነ​ባ​ች​ሁም ነበር፤ አሁን ግን እና​ያ​ለን ትላ​ላ​ችሁ፤ አታ​ዩ​ምም፤ ስለ​ዚ​ህም ኀጢ​ኣ​ታ​ችሁ ጸንቶ ይኖ​ራል” አላ​ቸው።


ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮስ ተነ​ሣና በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቆመ፤ መቶ ሃያ ያህል ሰዎ​ችም በዚያ ሳሉ እን​ዲህ አላ​ቸው።


እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፤ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፤ የቀደመውንም ኀጢአቱን መንጻት ረስቶአል።


ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤


ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።


አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።


የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።


ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች