Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ፍቅር ለዘ​ወ​ትር አይ​ጥ​ልም፤ ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ርም ያል​ፋል፤ ይሻ​ራ​ልም፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚ​ና​ገ​ርም ያል​ፋል፤ ይቀ​ራል፤ የሚ​ራ​ቀ​ቅም ያል​ፋል፤ ይጠ​ፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ነገር ግን ትንቢት ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ይሻራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ትንቢት የመናገር ስጦታም ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ያልፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ፍቅር ያለው ሰው ምንጊዜም አይወድቅም፤ ትንቢትን የመናገር ስጦታ ያልፋል፤ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ችሎታ ያልፋል፤ ዕውቀትም ቢሆን ያልፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 13:8
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ ኤዶ​ም​ያስ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴ​ማን ጥበብ የለ​ምን? ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችስ ምክር ጠፍ​ቶ​አ​ልን? ጥበ​ባ​ቸ​ውስ አል​ቆ​አ​ልን?


እኔ ግን ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ደ​ክም ስለ እና​ንተ ጸለ​ይሁ፤ አን​ተም ተመ​ል​ሰህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አጽ​ና​ቸው።”


በአ​ን​ጾ​ኪያ በነ​በ​ረ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ነቢ​ያ​ትና መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም በር​ና​ባስ፥ ኔጌር የተ​ባ​ለው ስም​ዖን፥ የቀ​ሬ​ናው ሉቅ​ዮስ፥ ከአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ከሄ​ሮ​ድስ ጋር ያደ​ገው ምናሔ፥ ሳው​ልም ነበሩ።


ጳው​ሎ​ስም እጁን በጫ​ነ​ባ​ቸው ጊዜ መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ነ​ርሱ ላይ ወረደ፤ ያን​ጊ​ዜም በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ተና​ገሩ፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገሩ።


ሁሉም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተሞሉ፤ ይና​ገሩ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እንደ አደ​ላ​ቸው መጠ​ንም እየ​ራ​ሳ​ቸው በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ይና​ገሩ ጀመሩ።


ለአ​ን​ዱም ተአ​ም​ራ​ትን ማድ​ረግ፥ ለአ​ን​ዱም ትን​ቢ​ትን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም መና​ፍ​ስ​ትን መለ​የት፥ ለአ​ን​ዱም በልዩ ዓይ​ነት ልሳን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም በል​ሳ​ኖች የተ​ነ​ገ​ረ​ውን መተ​ር​ጐም ይሰ​ጠ​ዋል።


ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ያ ተከ​ፍሎ የነ​በ​ረው ይሻ​ራል።


አሁ​ንም እነ​ዚህ ሦስቱ እም​ነት፥ ተስ​ፋና ፍቅር ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፤ ከሁሉ ግን ፍቅር ይበ​ል​ጣል።


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ትን​ቢ​ትን ለመ​ና​ገር ቅኑ፤ በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አት​ከ​ል​ክ​ሉት።


ዐወ​ቅሁ የሚል ቢኖር፥ ሊያ​ውቅ የሚ​ገ​ባ​ውን ገና አላ​ወ​ቀም።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ በፍ​ቅር የም​ት​ሠራ እም​ነት እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ም​ምና፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ም​ምና።


አዲስ ትእ​ዛዝ በማ​ለቱ የቀ​ደ​መ​ች​ቱን አስ​ረ​ጃት፤ አሮ​ጌና ውራጅ የሆ​ነ​ውስ ለጥ​ፋት የቀ​ረበ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች