17 ወደ ባልንጀራህ ቤት እግር አታብዛ፤ ታሰለቸውና ይጠላሃል።
17 እንዳይሰለቸውና እንዳይጠላህ፥ አዘውትረህ ወደ ባልንጀራህ ቤት አትሂድ።
17 ወደ ጐረቤትህ ቤት አዘውትረህ አትሂድ፤ ሊሰለችህና ሊጠላህ ይችላል።
ማር ስታገኝ በልክ ብላ፤ ከበዛ ያስመልስሃል።
በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር፣ እንደ ቈመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ተሳለ ፍላጻ ነው።
ይህን ዕቅድ ወደ እስጳንያ በምሄድበት ጊዜ ልፈጽመው ዐስባለሁ። በማልፍበትም ጊዜ ልጐበኛችሁና ከእናንተ ጋራ ለጥቂት ጊዜ ቈይቼ ናፍቆቴን ከተወጣሁ በኋላ በጕዞዬ እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ።