Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 9:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዓሉንም በዚህ ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ በተወሰነው ሕግና ሥርዐት መሠረት ሁሉ አክብሩ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በዚህ ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ፥ በተወሰነለት ጊዜ ታደርጉታላችሁ፤ እንደ ሥርዓቱ ሁሉ እንደ ደንቡም ሁሉ ታደርጉታላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚህ ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት በሕጉና በሥርዓቱ መሠረት ሥርዓቱን ይፈጽሙ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊ​ዜው አድ​ር​ጉት፤ እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ እንደ ፍር​ዱም ሁሉ አድ​ር​ጉት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በዚህ ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊዜው አድርጉት፤ እንደ ሥርዓቱ ሁሉ እንደ ፍርዱም ሁሉ አድርጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 9:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሁለተኛው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን በግ ዐረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ ዐፍረው ስለ ነበር ራሳቸውን ቀደሱ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አመጡ።


ንጉሡ፣ ሹማምቱና መላው የኢየሩሳሌም ጉባኤ የፋሲካውን በዓል በሁለተኛው ወር ለማክበር ተስማሙ።


ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ፋሲካን አደረገ፤ በመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካው በግ ታረደ።


እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን በግብጽ እንዲህ አላቸው፤


የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የእግዚአብሔር ፋሲካ በዓል ይጀመራል።


“እስራኤላውያን በተወሰነው ጊዜ የፋሲካን በዓል እንዲያከብሩ አድርግ፤


ስለዚህ ሙሴ ፋሲካን እንዲያከብሩ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤


እንዲህ ቢሆን ኖሮ፣ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ መከራን መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን በዘመናት መጨረሻ ራሱን መሥዋዕት በማድረግ ኀጢአትን ለማስወገድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተገልጧል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች