Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 7:88 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

88 ለኅብረት መሥዋዕት የቀረቡት እንስሳት ድምር ሃያ አራት በሬ፣ ስድሳ አውራ በግ፣ ስድሳ ተባዕት ፍየልና ስድሳ አንድ ዓመት የሆናቸው ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበር። እንግዲህ መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመሠዊያው መቀደስ የቀረቡ ስጦታዎች እነዚህ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

88 የአንድነትም መሥዋዕት ከብት ሁሉ ሀያ አራት በሬዎች፥ ስልሳም አውራ በጎች፥ ስልሳም አውራ ፍየሎች፥ ስልሳም የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ መሠዊያውን ለመቀደስ የቀረበ መባ ይህ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

88 ለአንድነት መሥዋዕት የቀረቡት የከብት ብዛት፦ ኻያ አራት ኰርማዎች፥ ሥልሳ አውራ በጎች፥ ሥልሳ ተባት ፍየሎች፥ ባለ አንድ ዓመት ዕድሜ ሥልሳ ተባት በጎች፥ መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቅደስ የቀረበ ቊርባን ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

88 የደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከብት ሁሉ፥ ሃያ አራት ጊደ​ሮች፥ ስድ​ሳም አውራ በጎች፥ ስድ​ሳም አውራ ፍየ​ሎች፥ ስድ​ሳም ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው የአ​ንድ ዓመት እን​ስት የበግ ጠቦ​ቶች ነበሩ። መሠ​ዊ​ያው ከተ​ቀባ በኋላ ለመ​ቀ​ደ​ሻው የቀ​ረበ ቍር​ባን ይህ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

88 የደኅንነትም መሥዋዕት ከብት ሁሉ ሀያ አራት በሬዎች፥ ስድሳም አውራ በጎች፥ ስድሳም አውራ ፍየሎች፥ ስድሳም የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቀደሻው የቀረበ ቍርባን ይህ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 7:88
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ እንከን የሌለው መሥዋዕት ያምጣ፤ ሥቡን፣ እስከ ጀርባ ዐጥንቱ ድረስ የተቈረጠ ላቱን በሙሉ፣ የሆድ ዕቃውን የሸፈነውን ሥብ፣ ከሆድ ዕቃው ጋራ የተያያዘውን ሥብ ሁሉ፣


ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑን ተክሎ ካበቃ በኋላ ማደሪያ ድንኳኑንና ዕቃዎቹን ሁሉ ቀባቸው፤ ቀደሳቸውም፤ እንደዚሁም መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ ቀባቸው፤ ቀደሳቸውም።


መሠዊያው በተቀባበት ቀን አለቆች የመሠዊያውን መቀደስ ምክንያት በማድረግ ስጦታዎችን አመጡ፤ በመሠዊያውም ፊት አቀረቡ።


መሠዊያው በተቀባ ቀን የእስራኤል አለቆች የመሠዊያውን መቀደስ ምክንያት በማድረግ ያቀረቧቸው ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፤ ዐሥራ ሁለት የብር ሳሕኖች፣ ዐሥራ ሁለት ከብር የተሠሩ ጐድጓዳ ሳሕኖችና ዐሥራ ሁለት የወርቅ ጭልፋዎች፣


ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረቡት እንስሳት የእህል ቍርባናቸውን ጨምሮ ድምራቸው፦ ዐሥራ ሁለት ወይፈን፣ ዐሥራ ሁለት አውራ በግ፣ ዐሥራ ሁለት አንድ ዓመት የሆናቸው ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሆነ፤ እንዲሁም ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡ ዐሥራ ሁለት ተባዕት ፍየሎች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች