ኢያሱ 8:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም33 እስራኤል በሙሉ መጻተኛውም ሆነ ተወላጁ፣ ሽማግሌዎቻቸውም ሆኑ ሹማምታቸው እንዲሁም ዳኞቻቸው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ተሸከሙት ሌዋውያን ካህናት ፊታቸውን አዙረው፣ በታቦቱ ግራና ቀኝ ቆመው ነበር። የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲባርኩ መመሪያ በሰጠ ጊዜ፣ አስቀድሞ ባዘዘው መሠረት፣ ግማሹ ሕዝብ በገሪዛን ተራራ፣ ግማሹ ደግሞ በጌባል ተራራ ፊት ለፊት ቆመ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 የእስራኤልንም ሕዝብ አስቀድሞ እንዲባረኩ የጌታ ባርያ ሙሴ እንዳዘዘ፥ እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ የአገሩ ተወላጆችም፥ መጻተኞችም፥ እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ለፊት ሆነው፥ የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 የእስራኤልን ሕዝብ እንዲባርኩ ቀደም ብሎ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እስራኤላውያን ሁሉና መጻተኞች ሽማግሌዎቻቸው፥ ሹሞቻቸውና ዳኞቻቸው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከተሸከሙት ከሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት ግራና ቀኝ እኩሌቶቹ ከጌሪዚም ተራራ ፊት ለፊት፥ እኩሌቶቹ ደግሞ ከኤባል ተራራ ፊት ለፊት ቆሙ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 የእስራኤልንም ሕዝብ አስቀድሞ ይባርኩአቸው ዘንድ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘ፥ እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ ጸሓፊዎቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ የሀገሩ ልጆችም፥ መጻተኞችም እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ አጠገብ፥ እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ አጠገብ ሆነው፥ የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ በተሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በግራና በቀኝ ቆመው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 የእስራኤልንም ሕዝብ አስቀድሞ ይባርኩ ዘንድ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘ፥ እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ የአገሩ ልጆችም፥ መጻተኞችም፥ እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ሆነው፥ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |