Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 8:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እስራኤላውያን የጋይን ወንዶች ሁሉ ባሳደዷቸው ሜዳና ምድረ በዳ ከጨረሷቸውና እያንዳንዳቸውንም በሰይፍ ከፈጁ በኋላ፣ ወደ ከተማዪቱ ተመልሰው በዚያ ያገኙትን ሁሉ ገደሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እንዲህም ሆነ፤ እስራኤልን ሊያሳድዱ ሄደው የነበሩትን የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ ከገደሉአቸው በኋላ፥ እነርሱም በሰይፍ ስለት እስኪያልቁ ድረስ ከፈጁአቸው በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ፥ በሰይፍም ስለት መቱአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እስራኤላውያን በሜዳና በምድረ በዳ ቀደም ሲል የዐይ ወታደሮች እነርሱን አሳደዋቸው በነበረው ስፍራ ሁሉንም ገድለው ከጨረሱ በኋላ ወደ ዐይ ከተማ ገብተው በዚያ የተረፉትንም በሰይፍ ፈጁአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተከ​ት​ለ​ዋ​ቸው በነ​በ​ረ​በት በተ​ራ​ራው ቍል​ቍ​ለ​ትና በም​ድረ በዳ የጋ​ይን ሰዎች መግ​ደ​ልን ከጨ​ረሱ፥ ሁሉ​ንም በጦር ወግ​ተው ከአ​ጠ​ፉ​አ​ቸው በኋላ ኢያሱ ወዲ​ያ​ውኑ ወደ ጋይ ተመ​ልሶ፥ በሰ​ይፍ አጠ​ፋት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እንዲህም ሆነ፥ እስራኤልን ሊያሳድዱ ሄደው የነበሩትን የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ ከገደሉአቸው በኋላ፥ እነርሱም በሰይፍ ስለት እስኪያልቁ ድረስ ከወደቁ በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ፥ በሰይፍም ስለት መቱአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 8:24
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እስራኤል ግን በሰይፍ መታው፤ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ድረስ ያለውንም ምድሩን ወሰደበት፤ ይሁን እንጂ የአሞናውያን ወሰን የተመሸገ ስለ ነበር ከያቦቅ አላለፈም።


ነገር ግን የጋይን ንጉሥ ከነሕይወቱ ይዘው ወደ ኢያሱ አመጡት።


በዚያች ዕለት የጋይ ሰዎች ሁሉ ዐለቁ፤ የወንዶቹና የሴቶቹም ብዛት ዐሥራ ሁለት ሺሕ ነበር።


ስለዚህም ጀርባቸውን አዙረው ከእስራኤላውያን ፊት ወደ ምድረ በዳው ሸሹ፤ ሆኖም ከጦርነት ማምለጥ አልቻሉም፤ ከየከተሞቹ የወጡ እስራኤላውያንም በዚያው ገደሏቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች