Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮናስ 4:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ፀሓይ ስትወጣ፣ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አመጣ፤ ፀሓዩም የዮናስን ራስ አቃጠለ፤ እርሱም ተዝለፈለፈ፤ መሞትም ፈልጎ፣ “ከመኖር መሞት ይሻለኛል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ፀሐይ ከወጣ በኋላ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ ላከ፤ የፀሐዩም ሐሩር ራሱን ስላቃጠለው ዮናስ ተዝለፈለፈ፤ ሞትንም በመመኘት “ከመኖር ይልቅ መሞት ይሻለኛል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትኩስ የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስን አዘዘ፤ ዮና​ስ​ንም እስ​ኪ​ዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራ​ሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮናስ 4:8
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም የቀጨጩና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁ ሰባት የእሸት ዛላዎች ወጡ።


በምድረ በዳም ውስጥ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዘ፤ ወደ አንድ ክትክታ ዛፍ እንደ መጣም፣ ከሥሩ ተቀምጦ፣ ይሞት ዘንድ “እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅቶኛል፤ እኔ ከቀደሙት አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰዳት” ብሎ ጸለየ።


ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ፣ “ዐፅመ ርስቴን አልለቅልህም” ስላለው፣ አክዓብ ተበሳጭቶና ተቈጥቶ ወደ ቤቱ ገባ፤ አኵርፎም በዐልጋው ላይ ተኛ፤ ምግብም መብላት ተወ።


እርሱም፣ “አነጋገርሽ እንደ ሞኝ ሴት ነው፤ መልካሙን ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀበልን፤ ክፉውንስ አንቀበልምን? አላት።” በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ በንግግሩ አልበደለም።


ስለዚህ እንዲህ ሆኖ ከመኖር፣ መታነቅና መሞትን እመርጣለሁ።


ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤ ጨረቃም በሌሊት ጕዳት አታመጣብህም።


ይህን ያደረግህ አንተ ነህና፣ ዝም እላለሁ፤ አፌንም አልከፍትም።


የሞኞች ቍጣ በዕቅፋቸው ውስጥ ስለ ሆነ፣ በመንፈስህ ለቍጣ አትቸኵል።


ጥቍር ስለ ሆንሁ ትኵር ብላችሁ አትዩኝ፤ መልኬን ያጠቈረው ፀሓይ ነውና፤ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ተቈጡኝ፤ የወይን ተክል ቦታዎችም ጠባቂ አደረጉኝ፤ የራሴን የወይን ተክል ቦታ ተውሁት።


አይራቡም፤ አይጠሙም፤ የምድረ በዳ ትኵሳት ወይም የፀሓይ ቃጠሎ አይጐዳቸውም። የሚራራላቸው ይመራቸዋል፤ በውሃ ምንጭ ዳርም ያሰማራቸዋል።


ነገር ግን በቍጣ ተነቀለች፤ ወደ ምድርም ተጣለች። የምሥራቅ ነፋስ አደረቃት፤ ፍሬዎቿንም አረገፈባት። ብርቱዎቹ ቅርንጫፎቿ ክው አሉ፤ እሳትም በላቸው።


በወንድሞቹ መካከል ቢበለጽግም እንኳ፣ የምሥራቅ ነፋስ ከምድረ በዳ እየነፈሰ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል፤ ምንጩ ይነጥፋል፤ የውሃ ጕድጓዱም ይደርቃል። የከበረው ሀብቱ ሁሉ፣ ከግምጃ ቤቱ ይበዘበዛል።


ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር፦ “ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡት መካከል፣ ቅድስናዬን እገልጣለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት፣ እከበራለሁ’ ብሎ የተናገረው ይህን ነው።” አሮንም ዝም አለ።


እግዚአብሔር ግን ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ አዘጋጀ፤ ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ዐደረ።


እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቢቱን አንገላታት፤ ልትሰበርም ተቃረበች።


አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ውሰድ፤ ከመኖር መሞት ይሻለኛልና።”


እግዚአብሔር ግን ዮናስን፣ “በውኑ ስለ ቅሉ ልትቈጣ ይገባሃልን?” አለው። እርሱም፣ “በርግጥ እስከ ሞት ልቈጣ ይገባኛል” አለ።


‘እነዚህ በመጨረሻ የተቀጠሩት አንድ ሰዓት ብቻ ሲሠሩ፣ ቀኑን ሙሉ በሥራ ስንደክምና በፀሓይ ስንንቃቃ ከዋልነው ጋራ እንዴት እኩል ትከፍለናለህ?’ አሉት።


እኔ የምወድዳቸውን እገሥጻለሁ፤ እቀጣለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ።


ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፤ ከዚህም በኋላ አይጠሙም፤ ፀሓይ አይመታቸውም፤ ሐሩሩም ሁሉ አያቃጥላቸውም፤


ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፣ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች