ኤርምያስ 17:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 በአገርህ ሁሉ ከተፈጸመው ኀጢአት የተነሣ፣ በምድሪቱ ያለህ ተራራዬ፣ ሀብትህንና ንብረትህን ሁሉ፣ መስገጃ ኰረብቶችህንም ጭምር፣ ለብዝበዛ አደርገዋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ! ባለጠግነትህንና መዝገቦችህን ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችህም ስለ ኃጢአት በድንበሮችህ ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 በመላ አገራችሁ በፈጸማችሁት ከፍተኛ ኃጢአት ምክንያት ያላችሁን ሀብትና ንብረት እንዲሁም መሠዊያዎቻችሁን ሁሉ በምርኮ ጠላቶቻችሁ እንዲወስዱ አደርጋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ! ባለጠግነትህንና መዝገብህን ሁሉ፥ የኮረብታውን መስገጃዎችህንም ስለ ኀጢአትህ በድንበሮችህ ሁሉ ለመበዝበዝ እሰጣለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ፥ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችህም ስለ ኃጢአት በድንበሮችህ ሁሉ ለመበዝበዝ እሰጣለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |